ከግርማ ጉተማ
የተስፋዬ ገብረዓብን አዲሱ መጽሃፍ "የኑረነቢ ማህደር" አነበብኩት። ቆንጆ መጽሃፍ ነው። መጽሃፉ በዋነኛነት ኑረነቢ በተባለ የሓልሓል ፋና መንደር ሰው (ኤርትራ) እና ቤተሰቦቹ እውነታኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ ከመሆኑ ባሻገር ባሉፉት 130 ዓመታት በምስራቅ አፍሪካ የተከሰቱና ያካባቢውን ህዝቦች በብዙ መልኩ አፌክት ያደረጉ ማህበረ-ፖለቲካዊ ኹነቶችን በተለይም ከሰሜኑ ጫፍ እይታ (from Eritreans perspective) አንጻር የቃኘ በመሆኑ ብዙ አዳዲስ ነገሮችን አግኝቼበታለው።
.
.
በተረፈ ግን...
ፊታውራሪ ገብርኤል ኤድሞንዶ (የኑረነቢ የልጅ ልጅ) የህይወት ታሪኩ ከጀነራል ታደሰ ቢሩ ጋር ተመሳስሎብኛል (ደራሲው ግን ይሄንን እውነታ አላጤነውም ወይም ለኣምባቢያን ማቅረብ አልፈለገም)። ቢያንስ ሁለት ምክኒያቶች ሁለቱን ሰዎች የሚያመሳስላቸው ይመስለኛል፥
1) ሁለቱም በወራሪው የጣሊያን መንግስት የሞቃዲሾ እስር ቤት የእድሜ ልክ እስረኛ ሆነው እንግሊዝ ጣሊያንን ከምስራቅ አፍሪካ እስካባረረችበት ጊዜ ድረስ ቆይተዋል።
.
2) ሁለቱም ለአጤ ሃይለስላሴ መንግስት በታሪክ የሚጠቀስ ውለታ የዋሉ ነበሩ።
.
.
ልዩነታቸው ደሞ ኦሮሞው ታደሰ ቢሩ ራሱ መልሶ በኢትዮጵያ መንግስት ላይ ያመጸ ሲሆን ኤርታራዊው ገብርኤል አድሞንዶ ግን ራሱ ሳይሆን ልጁ መኮንን ገብርኤል ነው ይሄን ያደረገው። በርግጥ አባቱም ደግፎታል በኋላ ላይ። ፊንፊኔ ላይ በዛ ዘመን እንደ ፈረንጅ ልጅ የራሱ ክፍል ውስጥ የምትኖር ውሻ የነበረው መኮንን፣ ሻዕቢያን በመቀላቀል ለኤርትራ ናጽነት ከ1976 እስከ 1982 (እኤአ) ደርግን በጦር ሜዳ ተፋልሞ 'ደንቦቢት' በተባለች ስፍራ ተሰውቷል። RIP!
በመጨረሻም፣ የኑረነቢ ማህደር ከተስፋዬ የሰጠ ያማርኛ ስነጽሁክ ክህሎት ጋር ተዳምሮ ባባቶቻችንና ባያቶቻችን ዘመን ፊንፊኔን ከኣስመራና ከሞቃዲሾ በማገናኘት ተሰርቶ የነበረው የጭቆናና ያገዛዝ እንዲሁም የፖለቲካ አሻጥር ትሪያንግል እንዴት ያለው ዘግናኝ እንደነበረ አንዳች ዓይነት ፍምጭ ለማግኘት ያስችለናል።
2 comments:
You are busy playing once again spying sherudly to create gaps among nationalities to poison Ethiopia. Be aware Habte Aba Mela is decedent of Amhara as he is Oromo. It is impo. to detach these nations. But l appreciate and thank U for the literary work U wrote about my father G. Tariku Ayiene. Be genuine. Thanks . Mekdela.

Post a Comment