“የኑረነቢ ማህደር” ታትሞ አልቋል። መጽሃፉ በካርቶን እየታሸገ ነው። በዋሽንግተን ዲሲ የምጽሃፍ ምረቃ ለማካሄድ ዝግጅት እየተደረገ ነው። ከሰኔ 1 2017 ጀምሮ መጽሃፉ www.amazon.com ላይ ለገበያ ይቀርባል። ተከታተሉን። ስለ ዴሞክራሲ፣ ስለ መጻፍ፣ ስለመናገር መብቶች እንታገላለን የሚሉ ወገኖች ከወዲሁ እንቅፋት ለመፍጠር በመሞከር ላይ መሆናቸውን ሰምቻለሁ። ስድብና እንቅፋትን የመቋቋም ልምድ ስላለለኝ አልደነቀኝም።
“የኑረነቢ ማህደር” መጽሃፍ እንዳይሰራጭ ተግተው በመስራት ላይ ያሉ ወገኖች ቀዳሚዎቹ አንባቢዎች እንደሚሆኑ ከልምድ አውቃለሁ። ካነበቡት በሁዋላ በልባቸው እንደሚወዱትም ርግጠኛ ነኝ። በተለይም በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል የተካሄደውን የስለላ ስራ ሲያነቡ በጸጥታ እንደሚደመሙ አውቃለሁ። ይህን መጽሃፍ ለማደናቀፍ በመሞከራቸውም ያፍራሉ። እፍረታቸውን ግን ለማንም አይናገሩም።
የመጽሃፌ
ውድ አንባብያን ሆይ! “የኑረነቢ ማህደር”ን ለማንበብ ጠረጴዛችሁን አጽዱ። እንደምትስቁ ርግጠኛ ነኝ። እንደምታዝኑና እንደምትገረሙም
አውቃለሁ። አንዳንድ ቦታ እንባ ይተናነቃችሁ ይሆናል። እንዲህ የሚሆነው የጻፍኩት ታሪክ መራር እውነት ስለሆነ ነው። “የኑረነቢ
ማህደር” ከእጄ ወጥቷል። ከዚህ በሁዋላ የኔ አይደለም።
2 comments:
ኣቶ ተስፋይ በታሪክ ሰሪዎቹ ይተተርከውን ታሪክ በመጣጥፋቸው ኣስውበው ስለ ኣቀረበልን ሳላመሰግነው ኣላልፍም:: የኣካባቢያችን ታሪክ በስማ በለው ትሪክ ጻሓፊዎችና ጋሽ ጃግሬዎቻቸው እንዳመቻቸው እያዛቡ በሚጋጭ መልኩ ለዘመናት ሲጻፉ ኑረዋል:: ታሪኩ ከኣፍ ታሪኩ፤ ተረቱ ከእውነቱ እየተደበላለቁብን ከትውልድ ወደ ትውልድ የትኛውን ኣቅበን የትኛውን እንደምንጥል ተደናግሮብን በምንድበዘበዝበት ዘመን እነሆ ኣንድልማድሕ በተዋቡ ቃላቶች ኣጅበሕ የኑረቢን ኣራት ትውልድ ታሪካዊ ጉዞ ጀባ ኣልከን:: ጀባ ይበልሕ::
ሰሎሞን ዘ ዲሲ
Post a Comment