Sunday, July 16, 2017

የግመል ጉዞ ልብ ይሞላል!

የካሊፎርኒያ ቆይታዬ በመጪው ማክሰኞ ይጠናቀቃል። ትናንት በኦሬንጅ ካውንቲ ጥሩ ቆይታ ነበረኝ። ዛሬ እሁድ ሎሰአንጀሊስ ላይ የውይይትና መጽሃፍ ላይ የመፈረም ስራ ይኖረኛል፡፡ ማክሰኞ በአወቶብስ ወደ ላስቬጋስ አቀናለሁ።
በዚህ ወር መጨረሻ የOSA ኮንፈረንስ ላይ ተሳትፌ ሳብቃ, ዳግም ወደ ሚኒሶታ እጉዋዛለሁ፡፡ ከ30ሺህ በላይ ኦሮሞዎች የሚገኙበት የስፖርት በአል ላይ መገኘት ያጉዋጉዋል፡፡ የኦሮሚያ ባንዴራ ጨረቃ መስሎ ሲውለበለብ ማየት ምን ያህል ልብ እንደሚነካ ለመረዳት የግድ ኦሮሞ መሆን ያስፈልጋል። ከሚኒሶታ ቀጥሎ ጉዞዬ ወደ አትላንታ ነው። የእውሮፕላን ትኬት ከወዲሁ ደርሶኛል፡፡
በመቀጠል ወደ ሲያትል አቀናለሁ፡፡ ቀናተኛ አድቃቂዎቼ በግንቦት ወር ሲያትል መግባቴን ቀደም ብለው የጻፉት እውነት አይደለም። ገና ልሄድ ነው። ከብዙ አመታት በፊት በዚህች ወብ ከተማ አሳ ማሸጊያ ፋብሪካ ውስጥ ወዛደር ሆኜ ሰርቻለሁ። ይኽው አሁን ዳግም ላያት ነው። ከሲያትል ቀጥሎ ወደ ቶሮንቶ ብቅ የማለት አሳብ አለኝ። ገና አልተረጋገጠም፡፡ የመጨረሻው ጉዞዬ ግን ሞስኮ ነው። ሞስኮ መሄዴ ካልቀረ ጎርኪይ የተወለደባትን ኒዥኒይ ኖቭጎሮድ, እንዲሁም ቮልጋ ወንዝን ማየት አለብኝ። በቅድመአያቱ በኩል የስጋ ዘመዴ ለሆነው ፑሽኪንም አበባ አኖርለታለሁ። ሩስያን የመጎብኘት አሳብ የነበረኝ ከአምስት አመታት በፊት ነበር። ሳይሳካልኝ ቆይቶ አሁን ግን ጊዜው ደረሰ።
ሰሞኑን ዜናዎችን ስፈታትሽ የኦሮሚያን በተለይ የአምቦን ቁጣ ሰማሁ፡፡ የወያኔ አድናቂዎች “መጣሁ!” እያሉ ላሽ ማለት ከጀመሩ ሰነባብተዋል። ሽምጥ እየጋለበ የሚመጣውን የኦሮሞ ህዝብ አብዮት ማቆም እንደማይቻል ከወዲሁ ለማወቅ ጠንቁዋይ መሆን አያስፈልግም። ሌላው ወሬ የእምቦጭ ጉዳይ ነው። ይህ አረም የጣና ሃይቅን ስለ መውረሩ የከረመ ዜና ቢሆንም ትልቅ ጉዳይ ሆኑዋል። ወያኔ እና እንቦጭ ተመሳሳይ ጠባይ እንዳላቸውም አነበብኩ። እመለስበታልሁ።

Sunday, July 9, 2017

ምነው ሁሉ እንዳንቺ አስመራ

"የኑረነቢ ማህደር" የተባለው አዲሱ መጽሃፌ ከሚተርካቸው ጉዳዮች አንዱ የአስመራን አመሰራረት ነው። በዚያን ዘመን አስመራን ለመገንባት የኤርትራውያን ጉልበት ባለመብቃቱ፣ የጉልበት ሰራተኞች ከሱዳን፣ ከየመን፣ ከአቢሲንያ፣ ከሶርያና ከኢጣልያ በሺህዎች መጥተው ነበር። አስመራን ሲገነቡ ህይወታቸው ያለፈ ቁጥር ስፍር የላቸውም። አስመራ ለዚህ ክብር መብቃትዋ ይገባታል። ዩኔስኮ ስላሳለፈው ውሳኔ የበለጠ ለማወቅ የኤልያስ አማረን ግድግዳ ይጎበኙ። Elias Amare

ሎሬት ጸጋዬ ገብረመድህን "እሳት ወይ አበባ" በተባለ የስነግጥም መድበሉ ስለ አስመራ ውበት የቁዋጠረው መወድስ እንዲህ የሚል ነበር፥
ምነው ሁሉ እንዳንቺ አስመራ
እንደ ከተሞች መዲና አቀያየሱ ቢጠራ
የአውራ ጎዳናሽ ጠለላ፣ ሁሉን ባክናፉ እየጠራ
አስር ሰአት ላይ ሲደራ
ለመንገደኛሽ መዝናኛ፣ ሲያጠላ፣ ሲያብብ፣ ሲያፈራ
ምነው ሁሉ እንዳንቺ አስመራ
አደባባይ ሲያነጥፉ
አድባራትና መስጊዱን፣ ካቴድራሉን በየረድፉ
ገበያውን በየመልኩ፣ እንደ አውታር እያሰለፉ
በወግ እየደረደሩ፣
በስምረት እያሰመሩ
በውበት እያዳብሩ
እያሳመሩ ቢያደሩ
በየክፍሉ፣ በየበሩ፣ በየመልኩ፣ በየተራ
ፋኖሱን እንደ ደመራ
ቡና ቤቱን እንድ ሶራ
ምነው ሁሉ እንዳንቺ አስመራ
እንደ ከተሞች መዲና አቀያየሱ ቢጠራ

Saturday, July 8, 2017

Oakland በዛሬው እለት


በዛሬው እለት የኤርትራውያን የኩዋስ ጨዋታ በአል Oakland ላይ በደመቀ ሁኔታ ተጠናቀቀ። በፎቶው ከኔ ጋር የምትታየው ኤልሳ ኪዳኔ ናት። Oakland በአሉ ላይ አብረን ዋልን።
የኦሮሚያውያን የኩዋስ ጨዋታ በአል ደግሞ ነሃሴ መግቢያ ላይ ሚኒሶታ ይካሄዳል። የOSAን ስብስባ ጨርሰን ስናበቃ ታጥቀን ጉዞ ወደ ሚኒሶታ ይሆናል። ዋቃ ጉራቻ ፈቃዱ ከሆነ በሚቀጥለው ጊዜ ቢሾፍቱ እንገናኛለን። “ኢጆሌ ዋራ ቢሾፍቱ” የተባለውን ገና ያልተዘፈነ ዘፈን እየዘፈንን “ሽው ወደ ቢሾፍቱ!” በውነቱ ፊንፊኔ አልናፈቀችኝም። “ከፊንፊኔ የትኛው ሰፈር ናፈቅህ?” ብባል ግን መልሴ ግልጽ ነው። “ዳካ-አራራ!” እላለሁ።