Tuesday, October 4, 2016

ቢሊሱማ በነፃ አይገኝም

ከተስፋዬ ገብረአብ (Gadaa)      
         
          የሰው ልጅ ይወለዳል፤ እንደ ዛፍ አርጅቶ ይሞታል። ስርአትም እንዲሁ፤ የተፈጥሮ ህግ ነው። ከመቶ አመታት በሁዋላ በህይወት የለንም። ሌሎች ግን ይኖራሉ። ታሪክ ብቻ ይቀራል። ጥይት ቢስተን ባይሎጂ አይስተንም። መስዋእትነት ሲከፈል ተተኪው ነፃነት መውረሱ አይቀርም። በቢሾፍቱ ከተማ፣ በሆራ አርሰዲ ደረት ላይ፤ በአድአ ጥቁር ሁዳድ - የተሰዋችሁ የኦሮሞ ልጆች - እንኳን ደስ ያላችሁ!! ታሪክ ሰርታችሁ - ታሪክ ሆናችሁዋል!!


          ዝንተ አለም ሲሞት ነበር ኦሮሞ! በማይመለከተው ጉዳይ! የራሱ ባልሆነ አደባባይ - ሲሰዋ ኖሯል ኦሮሞ። ቢሾፍቱ ላይ መውደቅ ምርቃት ነው። ከሆራ ደረት ላይ መንሳፈፍ ፀጋ ነው። በራስ አጀንዳ መሰዋት፤ በራስ መሬት ላይ መደፋት - ክብር እንጂ ሃዘን አይደለም። ቢሾፍቱ ለቄሮ አገሩ  ነው - አጀንዳው የራሱ ነው - ጋራና መልካው የግሉ ነው - ቢሰዋ ባገሩ ላገሩ ነው። አድአ በርጋ ስጋው ነው። ባቦጋያ ደሙ ነው። ፎቃ አያቱ ነው። የቱለማ እምብርት ነው። የበከጆ አባገዳ - የቁርቁራ ኩታገጠም - የኩሪፍቱ ገደም ገደም፤ ሲተኮስበት ባልባሌ፤ በእሬቻ እለት ዋዜማ - ማቅ ሲለብስ ኦሮሙማ - ከበሰቃ እስከ አዳማ - ከቱሉፈራ እስከ ጉምጉማ - ቄሮ ደረቱን ገልብጦ - ከበደገባቤ እስከ ሉጎ፤ ከበልበላ ሸምጥጦ - ሲሰዋ በሁዳዱ፤ ዋቃ ሁሉን ያይ ነበር - ጊዜ ይመጣል - አይዛነፍም ፍርዱ።

          ጭቋላ ከዋቃ በታች  - ሁሉን ያይ ነበር። ቄሮ ልቡ ሲበሳ በአረር - ከፉርጉጌ ጭምር። ከኢሉ አባቦራ የመጣ ቄሮ - ከመጫ የመጣ ቄሮ - ከቱለማዎች ሊውል አብሮ - ወጉን ሊያወጋ አድሮ - ከደንገጎ  የወረደ ጎረምሳ - ከሮቤ ወገኑ ሊያወሳ - ሊጫወት ዳንጋላሳ - ነበር አመጣጡ። ሌላ ጥያቄ አልነበረውም። ከቢሊሱማ ሌላ? - ከቶ ምን ጥያቄ ይኖረዋል? ትንሹ ጥያቄ እሱ ነው። ሲወለድ ጀምሮ - ያገኘው ከተፈጥሮ - ጥያቄው አንድ ነው - ከአምና እስከ ዘንድሮ!!

          የአግአዚ ጥይት ሲዘራ - እነ ቦንቱ ሲሳቀቁ - እነ ቄሮ ወርቁ - እነ ጋሜ ትጥቁ - ሞትን ንቀው ሲስቁ - እያወቁ ሲወድቁ - ምን ተሰማህ ጉዳ ሃይቅ ጥልቁ? ምን ተሰማህ ኪሎሌ - የእነ ጅሩ ጉርሜሳ ቀበሌ - ምን ተሰማህ አርሰዲ? ምን ተሰማህ የረር! የኦሮሙማ ሻኛ - የዋጂቱ አደ ማኛ - ነባር የቱለማ ዳኛ! ቄሮ ሲጋደም አጣምሮ መስቀለኛ!! ምን ተሰማህ ቢርማጂ? ቄሮ ሲወድቅ በደረቱ - ከእነ እህቱ - አደ ኦሮሞ ልጇ ሲወድቅ ተመትቶ፣ "ሌላም ልጅ አለኝ - የሚወድቅ" ብላ ስትናገር በቁጣ፣ ምንተሰማህ የፎቃው አባ ፊጣ? ምን ተሰማህ ቢሾፍቱ? እንግዶችህ ደጃፍህ ላይ ሲሞቱ? መቸም ሁሉን አይተሃል - ባይንህ በብሌኑ - ባይንህ በብረቱ። ቢሾፍቱ ልበ ጥልቁ - እስኪ የልብህን ንገረኝ? ሚሊዮናት ወገኖችህ አድአን ሲያጥለቀልቁ - በእሬቻ ዋዜማ ማታ - በአንድ ልብ ህብረ ቱማታ - በሰላም እየዘመሩ - ሲሳብባቸው ቃታ - በልበቢስ እሩምታ - ምን ተሰማህ ቢሾፍቱ!? ቢሊሱማን ለኩሳችሁ - በፀጥታ ያረፋችሁ - የምትኩ ልጅ አቦማ - የቱምሳ ልጅ ባሮ - የመዘምር ልጅ ማሞ - መንፈሳችሁ ተሳቀቀ? ወይስ ጊዜው እንደደረሰ ቆሌያችሁ አወቀ?

          እኔ ሩቅ ነበርኩ። ብቻ በሩቅ ሁሉን አያለሁ። ቢሾፍቱ በደም ስትታጠብ - የአግአዚ ጠመንጃ እሳት ሲታለብ - ጄኔራል ገብረዲላ ጨንቆት ሲካለብ - ሩቅ ሆኜ ታዘብኩ። ብቻዬን አልነበርኩም። እሬቻ አክብረን ስንመለስ - ከመልካ ጋር፣ ከኦሉማ ጋር፣ ከቀጄላ ጋር የእሬቻ ጠበል ልንቃመስ - አብረን ነበርን። ዜናው ሲሰማ - ኦሉማ አባ ቢሎ - ትንፋሽ አጣ ልቡ ቆስሎ። እኔም አየሁ - አቀርቅሬ - በማውቃቸው በእነዚያ ሰዎች - በእነ እፍረተቢስ አፍሬ - ሁሉን አየሁ በስጋት - የነገውን በቀል በመፍራት! የነገውን አደጋ በማሰብ - በጭንቀት!!

          የእንትና ልጅ እንትና - የእከሌ ልጅ እከሌ - የእንቶኔ ልጅ እንቶኔ - እባካችሁ ፈገግ በሉ - የኦሮሞ ልጆች ቀና በሉ። ማዘን አይገባም። በግልባጩ መቅናት ይገባል። ለቢሊሱማ ደረቱን የሰጠ ያስቀናል። በነፃ የሚገኝ ቢሊሱማ የለም። በጢኖ ሆራ ደረት ላይ የተንሳፈፈ ቄሮ - እድለኛ ነው። የዛሬ ጀግና ነው። የነገ ታሪክ ነው። የነገ ቢሊሱማ ነው።

               

12 comments:

Tesfaye said...

ሃዘንህ ተገቢ ነው፡፡ ለኦሮሞ ጠበቃ ከመሆንህ አንፃር የሲያንስ እንጂ አይበዛም፡፡ እኔንም አነባሁ፤አንተ ውስጥ ያለው ኦሮሞነት በማደግ፣አፈሩን በመፍጨት፣ውሃውን በመቦራጨቅ፣ልጅነትን በመጫወት እየተገነባ የመጣው የማንነት ተክለ ቁመናህ ነው ይህን ሁሉ እንድትል ያስገደደህ፡፡ እኔ ደግሞ ኦሮሞነት ከእናቴ በእትብት በኩል የተሰጠኝ ነው፡፡ መንፈሱ በሠራ አካላቴ ተዋህዶ ያለ፣ ልጣለው ብል፣ አሽቀንጥረ የሚጥለኝ፣ ልሸውደው ብል በደመነፍስ የሚያጋልጠኝ ማንነት፡፡ በደግነት፣በእውነት፣በርኀሩህነት፣በጨዋነት፣በአዛኝነት፣በሳቅ በጨዋታ ያሳደገኝ ማንነት፡፡ እኔ ግን ኦሮሞነት እንደ ገናሌ የሚፈስ፣ በረሃውን የሚያርስ፣ እንደ አዋሽ የሚያረሰርስ ማንነት ነው፡፡ ሳይንቲስቶቹ ዓለማት ተሠርተው አልተጠናቀቀም (The Universe is expanding) የሚል ዘገባ በየጊዜው ያቀርባሉ፤ አዳዲስ የሕዋ ግኝቶቻቸውም ለዚህ እየረዳቸው ነው፡፡ እኔ ኦሮሞነትን የማምነው በዚህ ስልት ነው፡፡ ብርሃን ጨለማውን እንደሚገልጠው ዓይነት ያለ መስፋፋት፣ በምሥራቅ አፍሪካ እጅግ ተስፋፊው፣ ተንሠራፊው ሕዝብ አድርጌ ነው የማየው፡፡ የኦሮሞ ሕዝብ በጠባቧ የኦሮሞ መሬት መውጫ መግቢያ ያጣ ሕዝብ አድርጌ አላየውም፡፡ ኦሮሞነት የሚቀጥለውን ሚለኒየም ስለማጥለቅለቁ ተስፋ ይኖረኛል፣ አማርኛ ግእዝንና አገውኛን ዘርሮ የገነነበትን የታሪክ ሂደት በእግጥ የሚያሳይ ምሑር ባይገጥመኝም፤ የቋንቋና የባሕል ተስፋፊነት ከዚያ ሕዝብ ጂኦግራፊያዊ ስምሪት ጋር የሚገናኝ መሆኑን ልብ ማለት ይገባል፡፡ እባክህ ኦሮሞነትን በኦሮሚያ ክልል ብቻ አትገድበው፣ ኢትዮትያዊነትን ከኦሮሞ ነጥለህ አትምታው፡፡ የኢትዮጵያ ታሪክ ተብሎ የሚተረከውን ልብ ብለህ ካስተዋልከው፤ በዚያ ታሪክ ውስጥ የወደቁትና ታላቅ ጀግንነት በመሥራት ከሚታወቁት ውስጥ በቁጥር የአንበሳውን ድርሻ የሚወስዱት ኦሮሞዎች ናቸው፡፡ ኢትዮጵያ በተበላሸ መሠረት ላይ የታነጸች ከሆነችም ይህን መሠረት (footing)በማቃናት የማእዘን ድንጋይ የሚሆነው ኦሮሞ መሆኑን መገንዘብ የሚያስቸግር አይመስለኝም፡፡ ይህ ከቁጥሩ ብቻ ጋር አይደለም፣ የኦሮሞ ሕዝብ መንፈሳዊ እሴቱ ሕብረ ብሔራዊነት (diversity) ነው፡፡ ጉዲፈቻ ዝም ብሎ የበቀለ ባሕል ይመስልሃል፡፡ ያንተ Gadda (በትክክል ከልጻፍኩት ይቅርታ) ዝም ብሎ የበቀለ ወፍ ዘራሽ ይመስልሃል? ከጥልቅ የኦሮሞ መንፈሳዊ እሴት የመነጨ ሁሉዐቀፍነት ባሕርዩ የሆነ በመሆኑ ነው፡፡

እባክህ ጠባቦቹ ሰፊውን፣ ሆደ ሰፊውንና፣ ገራገሩን የኦሮሞ ሕዝብ አቀጭጨው፣ አጽልመው "ጠባብ፣ የዋህ (ትክክለኛ ትርጉሙ ሞኝ ማለት ነው በነመለስ ወየኔ መዝገበ ቃላት)" በማለት የሚመጻደቁበትን የቃላት ድረታ አንተም እትካንበት፡፡ የወደፊቷ ኢትዮጵያ በምሥራቅ አፍሪካ ላይ ያላትን ወሳኝነት አስመልክቶ ያስነበብከንን መጣጥፍም አዋራ አታልብሰው፡፡

ምሥጋና የኦሮሞ ልጆች፣ መጽናናት በግፍ አገዛዝ ለረገፉ የኦሮሞ ንጹሑን፣ የአማራነት ሰለባዎች፣ የኦጋዴን ሶማሌ ጅምላ ተፈጂዎች፣ ለጋምቤላ አኙዋክና ኑዌሮች ሁሉ ይሁን፡፡

አሜን
ተስፋዬ

Anonymous said...

Hi Abba Gedda,
I really thank you for your thoughtful, compulsive, moral boosting and heroic linguistically rich post on the tragedy at Bishoftu. We love you brother. Keep it up as always.
Your old Finfine friend,
Ashebir Getachew.
Houston, Texas, USA.

Anonymous said...

I'm an Eritrean Citizen from Australia but from this moment I'm oromo. The massacre of the erecha ceremony changes everything. I'm calling to all Eritrean brothers and sisters in Australia to share all the photos of the people of oromo who killed by the weyane AGAZI soldiers to every Australian citizen you know in the social media. I share this massacre with my friends in Uni and facebook. Let's give our voice to the voice less.

Anonymous said...

Loving it..my man..Gadaa!!!

Anonymous said...

Congratulations!? This must be the blood feast you and your Shabia masters have been hoping for a long time

Ted Gebregzi said...

It is long time ago,I was watching television in a house of an African who wasliving with a dutch woman in Amsterdam and at that very moment,I was watching a documentary of Martin Luther King,I was fresh from Ethiopia,I wasn'r yet spoiled by dbad frioend and drinks,i never forget that evening,tears were flowing my face.

Ted Gebregzi said...

It is long time ago,I was watching television in a house of an African who was living with a dutch woman in Amsterdam and at that very moment,I was watching a documentary of Martin Luther King,I was fresh from Ethiopia,I wasn't yet spoiled by bad frioend and drinks,I never forget that evening,tears were flowing my face.

Raaga Amantaa said...

Let Waaqaa bless you and give you chance to see freedom of OROMIA!
Just Thanks!

Anonymous said...

We did that we share that in the UWA.
Also we need to say shame on you to the Australian media for not broadcasting this. What is the difference between the massacre in soria and the massacre of oromo people in ethiopia. We need to sign and collect petition to send to the highest office.

Daniel

Anonymous said...

Good job Daniel. This is a big lesson to the weyane dictators. Our Eritrean brothers are in our side. Until freedom coming we will fight weyane.

Anonymous said...

i Hate to read you ,but i can't help it.

Anonymous said...

ተስፋዬ ገብረአብ

r u going to join the war effort or you only wish the poor to die fo you