ሃይሌ ገብረስላሴ ላይ ሰሞኑን በወረደበት ድብደባ
በጣም ተገርሜያለሁ። ሃይሌ የፖለቲካ ሰው አይደለም። የተናገረው የአፍ ወለምታም ሊሆን ይችላል። በፖለቲካው በኩል ተፅእኖ የማድረግ
ችሎታውም ያን ያህል አይደለም። ምንድነው ይሄ ሁሉ ጩኸት? ደግሞስ ምን ስህተት ተናገረ?
የፖለቲካ ሳይንቲስት የሚባሉ ስንቶቹ አስተሳሰባቸው
የማጅራት መቺ መሆኑ ይታወቃል። ወያኔን በፀረ ዴሞክራሲያዊነት ኪሚከሱት መካከል ግማሾቹ ከወያኔ የባሱ አፋኞች ናቸው። መመፃደቅ
ምን ያደርጋል? ዴሞክራሲ እኮ ባህል ነው። ከአንደበትህ ከሚወጡት ቃላት ይጀምራል። መሳደብ ፀረ ዴሞክራሲ ነው። ከዚያም አልፎ ብልግና
ነው። ባለጌና ስድ ከመሆን እንደ ሃይሌ በአሳብ መሳሳት የተሻለ ነው።
በጠሉት ሰው ላይ የሞት ፍርድ ሲፈርዱ የሚውሉ ስንቶች ናቸው?
ስልጣኑ ባይኖራቸውም የመናገርና የመፃፍን ነፃነት ለማፈን የሚተጉ ስንቶች ናቸው? ሃይሌ በርግጥ አነጋገሩን አላወቀበትም። ማለት
የፈለገውን በተሻለ መንገድ ማለት እየቻለ እንደ ፊጋ በሬ ሄዶ ከግድግዳ ተጋጨ። አባባሉን “በመልካም አስተዳደር በኩል ዴሞክራሲያዊ
ባህላችንን ማዳበር ይገባናል” በሚል ማረም ይቻል ነበር። “የለም! አቋሜ ነው። ለአፍሪቃ ዴሞክራሲ አያስፈልጋትም!” ብሎ የሚፀና
ከሆነም መሰደብና መዋረድ የለበትም። በግልፅነት አሳቡን መናገሩ ሊከበርለት በተገባ። (Gadaa)
1 comment:
THANK YOU!!! "THE BLACK SOIL OF ADHA"
Post a Comment