Friday, February 19, 2016

ከኦሮሞ ማዕበል ማግስት …

        በአለማችን ላይ ወጣቶች በአንድ ልብ የተሳተፉበት ያልተሳካ የአብዮት ታሪክ አናውቅም። የጊዜ ጉዳይ ብቻ ነው። ይህችን እየፃፍኩ ሳለ የማያቋርጥ፣ የተቀናጀ የአመፅ ዜና ከኢትዮ - ኦሮሚያ እየሰማሁ ነበር። ዝምታው ማብቃቱ ግልፅ ነበር። የኦሮሚያ ወጣቶች የስርአቱን ታጣቂ ሃይል በጦርና በጠመንጃ ይፋለሙት ይዘዋል። ከሻሸመኔ ወደ አዲስአበባ መንገድ ተዘግቶአል። ልማደኛዋ ኮፈሌ ጦርሜዳ ሆናለች። ብረት ለበስ ጦር ኮፈሌና ሻሸመኔ ገብቷል። በጥቅሉ ወለጋና ሃረርጌ ፀጥታ የለም። ሱሉልታ ብሶበታል። ጭራሽ ገበሬዎቹ ያስለቀቁትን መሬት መከፋፈል ጀምረዋል። ደራ ነፃ ነው።
አጄ ሃራ ነው። ጅማ መስመር አምቦና ጉደር መንገዱ ዝግ ነው። ሮቤ፣ ጉጂ፣ ቡሌሆራ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ጋሼራ፣ አሊ፣ ጃርጋዳ፣ እነዚህ ሁሉ ነፃ የወጡ መንደሮች ናቸው። ወያኔ ወደ ኦሮሚያ ገጠሮች መንገድ አለመዘርጋቱ አሁን ጠቀመ። የፌደራል ፖሊስ መኪናውን ገትሮ በእግር ሲንቀሳቀስ ለኢላማ ተጋለጠ። እንደ ቅዱስ ጊዮርጊስ ጦር ሲተከሉ ብቻ የሚታዩ ጦሮች የፌደራል ፖሊስን ሲጥሉ ታዩ። አሜሪካና ኖርዌይ ዜጎቻቸው በደቡብና በኦሮሚያ በሚያደርጉት እንቅስቃሴ ላይ ገደብ ጥለዋል። የቱ ተነስቶ የቱ ይተዋል? መንገድ መዝጋት የመሳሰለው የአመፅ ድርጊት ስለተለመደ ዜና መሆኑ ቀርቶአል። አመፁ እንደ ሰደድ እሳት እየተቀጣጠለ ነው። እንደሚቀጥልም ይጠበቃል።  

ርግጥ ነው፤ ሊነጋ ሲል ሁሉም ያውቃል። አርጅቶ ይወድቃል - ስርአትም እንደ ዛፍ። የመኖር ግዳጁን ይፈፅማል። እንደምንታዘበው ከሆነ ሁለት አይነት የህወሃት አባላት አሉ። የአዲሳባ እና የመቐለ ተብለው ይለያሉ። የመቐለ የህወሃት አባላት ግራ ተጋብተው ዝምብለው በመገረም ይመለከታሉ። ለራሳቸው ምንም የላቸውም። እንደ ግለሰብ የተረፋቸው ሃሜት እና ጥላቻ ብቻ ነው። ባልዋሉበት መታማት ለቁጭቶች ሁሉ ቁጭት ይዳርጋል። የአዲሳባዎቹ ወያኔዎች ከመሬት ሽያጭ በሚገኝ ገንዘብ ሰክረው የሚያደርጉትን አያውቁም። አንዳንዶቹ ከመኪና ማቆሚያቸው ምድር ቤት፤ ሁለተኛ ፎቅ ላይ ወደሚገኘው መኝታ ቤታቸው ለመሄድ አሳንሰር ይጠቀማሉ። ዳሩ እንደነበሩ መቆየት የለም። ጊዜው ሲደርስ የነበረው እንዳልነበረ ይሆናል። እና “የመኖር ግዳጁን ወያኔ ፈፀመ?” ብለን ለመጠየቅ እንገደዳለን። በርግጥ፤ እየተንገዳገደም ቢሆን ጥቂት ይጓዝ ይሆናል። ነዳጅ አልቆበት ሳለ በቁልቁለት መንገድ ላይ እንደሚጓዝ መኪና ቁጠሩት።

የኦሮሞን ህዝብ አመፅ ማፈን እንደማይቻል ካመንን፤ ወያኔም የመኖር ግዳጁን እንደፈፀመ ከገመገምን ስለ መጪው ዘመን በግልፅ መነጋገር ይገባል። ምክንያቱም የወያኔ መውደቅ ብቻውን ድል አይደለም። የነበረውን ስታነሳ፤ በቦታው ምን ለመተካት አቅደሃል? ወያኔን ከማስወገዱ ባላነሰ ሁኔታ ከባዱ ፈተና መጪውን ዘመን የተሻለ ማድረግ ስለመቻሉ ሆኖ ቆይቶአል። የሚፃፉ ፅሁፎችን ስንታዘብ በጥቅሉ በአማራ እና በኦሮሞ ልሂቃን መካከል ከወዲሁ ሽኩቻ የተጀመረ ይመስላል። ይህ ሽኩቻ ለጊዜው የተሟላ እልባት ማግኘት ባይችል እንኳ፤ የማቀራረቢያ የጋራ ጥርጊያ ካልተበጀለት ወያኔ ቀዳዳዋን በመጠቀም በስልጣን ለመቆየት አንድ የመጨረሻ እድሉን ሊሞክር ይችላል።   

ግርማ ካሳ የተባለ ፀሃፊ በቅርቡ “ዘሃበሻ” ድረገፅ ላይ የፃፈው ፅሁፍ ትኩረቴን ለመሳብ በቅቶ ነበር። ፀሃፊው በመጣጥፉ ኦሮሞነት የሚለካበት መንገድ ምን እንደሆነ ይጠይቃል። አብነት ለመስጠትም ስለ ራሱ የዘር ሃረግ እንዲህ ሲል በዝርዝር ገለፀ፣

“… እኔ አንድ አያቴ ከቦረና (ኦሮሞ) ሁለተኛ አያቴ ከወለንጭቲ (ኦሮሞ) ነበሩ። ሶስተኛ አያቴ አባታቸው ከሸንኮራ (ሸዋ) የነበሩ ሲሆን፣ እናታቸው ደግሞ የጂማ ኦሮሞ ነበሩ። አራተኛው አያቴ ከጎጃም ናቸው። እንደሚታወቀው ጎጃም አማርኛ ይናገር እንጂ ከኦሮሞ ጋር የተደባለቀ ነው። ወለጋ እንደማለት ነው። እኔ ቢያንስ 5/8 ኦሮሞ ነኝ። ሮሞነት በቋንቋ ከሆነ አፋን ኦሮሞ ተናጋሪ አይደለሁም። አፋን ኦሮሞ አለመናገሬ ደግሞ ፈልጌ ያመጣሁት አይደለም። ኦሮሞነት ኦሮሚያ በመወለድ ከሆነ ኦሮሚያ እምብርት ፊንፊኔ በመወለዴ ኦሮሞ ነኝ…”

ግርማ ካሳ 5/8ኛው ኦሮሞ መሆኑን አስረድቶን ሲያበቃ በኢትዮጵያዊነት መጠራት እንደሚፈልግ ገልፆአል። እንደሚመስለኝ ችግር እየተከሰተ ያለው እንደ ግርማ ካሳ ያሉ ወገኖች አርባ ሚሊዮን የሚሆነውን የኦሮሞ ህዝብ “እንደኛ ካላሰብክ፣ እንደኛ ካላመንክ፣ እንደኛ ካልለበስክ!” ሲሉ ደጋግመው መዛታቸው ነው። ዛቻቸውን አሰልቺ የሚያደርገው ደግሞ የማስገደድ አቅማቸው ተረት ሆኖ መቅረቱን አለማወቃቸው ነው። ግልፅ ለማድረግ ያህል ግን ኦሮሞ ማነው?” ለሚለው ጥያቄ ያነበብኳቸውን የኦነግና የሌሎች ኦሮሞ ነክ ድርጅቶች ሰነዶችን በማጣቀስ በቀላሉ ምላሽ ለመስጠት ልሞክር፣

1) - በእናቱም በአባቱም ከኦሮሞዎች የተወለደ ኦሮሞ ነው። ለአብነት ጢኖ ባሮ፣ ትዝታ በላቸው፣ ቶሌራ አዳባ፣ ህዝቅኤል ጋቢሳ፣ አባጫላ ለታ፣ ሃሰን ሁሴን፣ ሩንዳሳ አሼቴ፣ ወርቅነሽ ቡልቶ፣ በያን አሶባ፣ ጥሩነሽ ዲባባ፣ የሺ ቶሎሳ፣ ሌንጮ ባቲ፣ ትእግስት ገሜ፣ ጃዋር መሃመድ፣ ዋሚ ቢራቱ፣ ሃጫሉ ሁንዴሳ፣  ጃምቦ ጆቴ፣ ገላና ጋሮምሳ፣ ሴና ሰለሞን፣ ጃፈር ዩሱፍ፣ ጄኔራል አለምሸት ደግፌ፣ ሃዊ ተዘራ፣ በቀለ ገርባ፣ ሲፈን ጫላ፣ እያልን ስንቀጥል ከአርባ ሚሊዮን በላይ መመዝገብ ይቻላል።  

2) - በእናቱ ወይም በአባቱ በግማሽ ወይም በእሩብ ኦሮሞ የሆነ ሁሉ ኦሮሞ ነው። ወይምኦሮሞ ነኝ’ የማለት መብት አለው ለአብነት አንዳርጋቸው ፅጌ፣ ነአምን ዘለቀ፣ ሃይሉ ሻውል፣ ያሬድ ጥበቡ፣ ብርቱካን ሚደቅሳ፣ ነገደ ጎበዜ፣ ጄኔራል ሰአረ መኮንን፣ ዶክተር ትእግስት መንግስቱ ሃይለማርያም፣ ኩማ ደመቅሳ፣ አትሌት ሃይሌ ገብረስላሴ፣ ኢንጂነር ግዛቸው ሽፈራው፣ ግርማ ሰይፉ፣ ቴዲ አፍሮ፣ በዕውቀቱ ስዩም እነዚህን የመሰሉ በከፊል ኦሮሞዎች ፍላጎታቸው እስከሆነ ድረስ  ኮርተው ኦሮሞ ናቸው።

3) - የኦሮሞ ህዝብ በባህላዊ መንገድ ኦሮሞነትን በአክብሮት የሰጣቸው ግለሰቦች ሁሉ ኦሮሞ ናቸው። ለአብነት ፕሮፌሰር አስመሮም ለገሰ (ሃዩ) ዶክተር ቦኒ ሆሎኮም (ቃበኔ) ተስፋዬ ገብረአብ (ጋዳ) ዶክተር ትሩማን እና ሌሎችም ሊጠቀሱ ይችላሉ።

ከዚህ ውጭ ኦሮሚያ ላይ ስለተወለደ ወይም ኦሮምኛ ቋንቋ አቀላጥፎ ስለቻለ አንድ ግለሰብ ኦሮሞ ሊባል አይችልም። እንደተረዳሁት ከሆነ ከላይ በተጠቀሱት ነጥቦች OPDO ባላውቅም ሌሎች ኦሮሞ ነክ ፖለቲካ ድርጅቶች ሁሉ ይስማማሉ። አንድ ግለሰብኦሮሞ ነኝለማለት ከእነዚህ ሶስቱ መንገዶች በቀር ሌላ ቀዳዳ፣ ሌላ መስኮት፣ ሌላ በር፣ ሌላ የዘመድ-በር ወይም ሌላ የዘመድ-መስኮት ያለ አይመስለኝም ሌሎች ኢትዮጵያውያን በተለያዩ መመዘኛዎችየኦሮሚያ ዜጋመሆን ግን ይችላሉ። በኦሮሚያ ክልል መሬት ላይ የተወለደ ሁሉ በቀጥታ ኦሮሞ መሆን ባይችልም የኦሮሚያ ዜጋ መሆን ይችላል። ማለትም በኦሮሚያዊ ዜግነት ሲኖር በእናት ቋንቋው የመጠቀም፣ የመምረጥና የመመረጥ፣ ሃብት የማፍራት መብቱ ያለገደብ ይከበርለታል። እድሉን ካገኘ ደግሞ በሞጋሳ ባህል ኦሮሞ መሆን ይችላል። ከዚህ ባሻገር ከኦሮሚያ ጋር ኩታገጠም የሆኑ አናሳ ብሄረሰቦች ባህላቸውና ቋንቋቸው ተከብሮላቸው የኦሮሚያ አካል መሆን ይችላሉ። ኦሮሚያ ሳይወለዱ የኦሮሚያ ነዋሪ ሆኑ ወይም የተጋቡ ደግሞ በጥያቄያቸው መሰረት የኦሮሚያዊ ዜግነት ሊሰጣቸው ይችላል።

ይህ ሊሆን የሚችለው እንግዲህ ኦሮሚያ ነፃነቷን አውጃ ሉአላዊት አገር ከሆነች ነው። ፊንፊኔን ይዛ ኦሮሚያ ነፃነቷን ካወጀች እሱን ተከትሎ ደቡብ ህዝቦችና ኦጋዴንያ ከኦሮሚያ ጋር ሊፈጥሩት የሚችሉት በጋራ ጥቅም ላይ የተመሰረተ ስምምነት ሊመጣ ይችላል። እስካሁንም እንዲህ ያለ ርእሰ ጉዳይ አልተነሳም ማለት አይቻልም። 2014 ላይ ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ OSA ኮንፈረንስ ላይ ተገኝቶ ያደረገው ንግግር አግጣጫ ጠቋሚ ነበር። የኦሮሞ ህዝብ ከደቡብ ህዝቦች ጋር የተጋራውን ታሪክና ባህል አንስቶ የተቀናጀ ትግል ማድረግ እንደሚያስፈልግ አሳስቦ ነበር። የቤኒሻንጉልና የጋምቤላ ንቅናቄዎች ከኦሮሞ ግንባሮች ጋር ያላቸው ረጅምና ታሪካዊ ትብብርም ስትራቴጂያዊ ነው። ወያኔ ራሱ እንደሚያስወራው ከበጌምድር፣ ከአፋርና ከወሎ ሰፋፊ ውሃገብ መሬቶችን ወስዶ “ሰሜን ኢትዮጵያ” የተባለች አዲስ አገር ለመመስረት ቢንቀሳቀስ (አውራምባ ታይምስ - ቃለመጠይቅ ከአብርሃም ያየህ ጋር)  ኦሮሞ የኢትዮጵያን ግዛት ለማስከበር ወደ አክሱም ይዘምታል ተብሎ አይታሰብም። ይህ ፅሁፍ ቅዠት መስሎ የሚሰማው ወገን ሊኖር እንደሚችል አውቃለሁ። ቅዠት መስለው ይታዩ የነበሩ በርካታ አጀንዳዎች ሲፈፀሙ ግን አይተናል። በኛው ዘመን፤ በኛው እድሜ አይተናል። 

እንግዲህ እዚህ ደረጃ ላይ ገና አልተደረሰም። ከወያኔ የመኖር ግዳጅ ማብቃት በሁዋላ ጉዞው ወደዚያ አግጣጫ መሆኑን ለማሽተት ግን ፖለቲከኛ መሆን አይጠይቅም። ያም ሆኖ አሁንም ቢሆን ሁሉም ዜጋ በአንድ ብሄራዊ ማንነት ሊታወቅ የሚችልባት አንዲት ታላቅ ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን ለመመስረት የሚቻልበት እድል የተዘጋ አይመስለኝም። በቅድሚያ ግን አደጋ ላይ የወደቀውን የኢትዮጵያ አንድነት እንደነበረ ለማቆየት የኦሮሞ ህዝብ ሚና ወሳኝ መሆኑን ማመን ይገባል። ወሳኝ ስል የአንበሳ ድርሻ ማለቴ ነው።

በትክክል የኦሮሞ ህዝብ ከፊቱ ሁለት ምርጫዎች አሉት። እነርሱም “የኦሮሚያን ነፃ ሪፖብሊክ ማወጅ” ወይምበኢትዮጵያዊነት ማእቀፍ ስር የኦሮሚያን ክልል መቀበል” ናቸው። የኦሮሞ ህዝብ ከሁለት አንዱን የመምረጥ ብቃቱን እያረጋገጠ በመሄድ ላይ ይገኛል። ከእነዚህ ሁለት ምርጫዎች ባሻገር ሌላ አማራጭ የለም። ፕሮፌሰር መሳይ ከበደ በግልፅ እንዳስቀመጠውሌላ አማራጭ አለከተባለ ጦርነት ነው። ጦርነት ከተነሳ ውጤቱ ምን እንደሚሆን ለመገመት አያዳግትም። የጦርነት አማራጭ ለሁሉም ወገን አደገኛ ነው። ለኢትዮጵያ ጎረቤት አገራት ጭምር በጣም አደገኛ ነው። እና ጦርነቱን አለማሰብ ይበጃል።

የኦሮሞ ህዝብ የሚፈልገውን እንዲመርጥ እድል መስጠት ወሳኝ ጉዳይ ይመስለኛል። ለስኮትላንድ ህዝብ የተሰጠው የመምረጥ መብት ለኦሮሞ ህዝብ የማይሰጥበት ምክንያት ምንድነው? በዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ ውስጥ የኦሮሞ ህዝብ ይበልጥ ተጠቃሚ ሊሆን እንደሚችል ማሳመን መቻል አስተማማኝ ሰላም ያስገኛልማነው ኦሮሞ?” በሚለው ጥያቄ ውስጥእኔ ኦሮሞ ነኝየማለት መብት ያላቸው ወገኖች ለኦሮሞ ህዝብ ጥያቄዎች ያላቸውን በጎ ራእይ ቀረብ ብለው መግለፅ ይችላሉ። መሳይ ከበደ የኦሮሞን ህዝብ ጥያቄ በመቀራረብ መፍታት እንደሚቻል ማመኑ፣ እምነቱንም በግልፅ በመፃፉ ምን ያህል ኦሮሞ ደጋፊዎችን እንዳፈራ በቅርቡ ያየነው ነው። መቀራረብ ይቻላል። በአንድነት መኖር ይቻላል። ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን መገንባት ይቻላል። መልካም አስተዳደርን ማስፈን ይቻላል።

የኦሮሞ ህዝብ ወደ ሪፈረንደም ከመግባቱ በፊት በመካከሉ ረጅም የሽግግር ጊዜ ሊኖር እንደሚችል ግልፅ ነው። በዚህ የሽግግር ጊዜ እውነተኛው ዴሞክራሲ ከታየ ውጤቱ ተገላቢጦሽ ሊሆን ይችላል። የኦሮሞ ህዝብ የራሱን አገር ያውጃል ብሎ ከመስጋት ይልቅ፤ ከኢትዮጵያ ጋር በፌዴሬሽን ሊቀላቀሉ የሚሹ የአካባቢ አገራት ፍላጎት በርትቶ ሊታይ ይችላል ብሎ ማሰብ የሚቀል ይመስለኛል። ምክንያቱም ፍትህ፣ ዴሞክራሲና እኩልነት የሰፈነበት ትልቅ ህብረት ውስጥ አካል መሆን የማይመኝ የለም

Gadaa Ghebreab የቅዳሜ ማስታወሻ www.tgindex.blogspot.com ttgebreab@gmail.com feb. 18 2016

17 comments:

Unknown said...

ተስፍሽ.አኖሌ ዋቆ ከኤርትራ ወደ ኦሮምያ ሳይገባ አልቀረም። የሀወኒም ድጋፍ ያለበት ይመስላል።

Unknown said...

ተስፍሽ.አኖሌ ዋቆ ከኤርትራ ወደ ኦሮምያ ሳይገባ አልቀረም። የሀወኒም ድጋፍ ያለበት ይመስላል።

Unknown said...

ተስፍሽ.አኖሌ ዋቆ ከኤርትራ ወደ ኦሮምያ ሳይገባ አልቀረም። የሀወኒም ድጋፍ ያለበት ይመስላል።

Anonymous said...

Believe me;you won't die before you see the disintegration of 'your fake state' and its plea to Ethiopia for help.

Anonymous said...

"አይ ተስፋዬ…!!" አለ አላሙዲን። አንተ በቃ ትቃዣለህ…?! ዐማራ ኢትዮጵያን የተቆጣጠረ‘ለት ግን፣ ዛሬ አንዳርጋቸው በወያኔ ተቀፍድዶ እንደመጣው ተቀፍድደህ ትመጣለህ። ያኔ አንተን አያድርገኝ! ወዮልህ!! ወደድክም ጠላህም ቀጣዩ የኢትዮጵያ አስተዳዳሪ ዐማራ ነው። ያኔ ታዲያ ያንተ ሞገሳ፣ ገዳ፣ ጓዳ፣ እገዳና ግድግዳ ገደል ይገደገዳል። ይሄ ሁሉ ድካምህ በሽተኛነት ይሆናል። ይመችህ!!

Anonymous said...

I agree with you that marginalizing the Oromo must end once and for all. The Oromo have been sacrificing their blood, their lives, their sweat and their limbs/ organs for territorial integrity and sovereignty of Ethiopia. After all Ethiopia is not the product of expansionist Atse Menilik alone, but also the collaborative works of the brave warlords of Oromo who had envisioned the purpose of one united nation for peaceful and lasting existence.

I know one thing in communication theory that any writer has the power of wit to influence or allure the audience's intention of interpretation the same way as the writer’s preconceived intention. In this context your article is sort of fuel on fire deemed to set ablaze the Oromo disobedience to take another paradigm pushing them to be captive of historic oppression of the past.

I am one of the half cast you have mentioned in the second order of the definition of who is supposed to be Oromo. But I have never ever had a time I think of my self without Ethiopia.

I know you are committed in supporting the struggle to end the unfair treatment and marginalization of the Oromo’s from social, political and economic rights and benefits. With this in mind I thumped up for your wonderful effort and solidarity in this hectic time of hardship.

If we are destined to session, that is how it ends up. But, please do not be the immediate cause; do your best and take the positives out of the struggle in building a nation of diversity to be glamorously represented by unique identity, observation and exercising of human rights.

Regards,
Tesfaye

Unknown said...

I am Oromo and carefully know the psychological make up our people, Oromo is not a threat for Ethiopia Unite rather an opportunity to bring sustainable stability once it come to power.Many thanks Obbo Tesfaye your analysis is perfect and you will see the result soon.


Anonymous said...

In many parts of Oromiya, no school, Oromo youngsters are killed everyday. Yours are attending class. My "Unity Hero" Amharas, where is yr stand with us if u really care for Ethiopia

Anonymous said...

why don't you focus on the idea you have brought late in your article: "መቀራረብ ይቻላል። በአንድነት መኖር ይቻላል። ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን መገንባት ይቻላል። መልካም አስተዳደርን ማስፈን ይቻላል። የኦሮሞ ህዝብ የራሱን አገር ያውጃል ብሎ ከመስጋት ይልቅ፤ ከኢትዮጵያ ጋር በፌዴሬሽን ሊቀላቀሉ የሚሹ የአካባቢ አገራት ፍላጎት በርትቶ ሊታይ ይችላል ብሎ ማሰብ የሚቀል ይመስለኛል። ምክንያቱም ፍትህ፣ ዴሞክራሲና እኩልነት የሰፈነበት ትልቅ ህብረት ውስጥ አካል መሆን የማይመኝ የለም።"

Anonymous said...

First of all your definition of who is oromo is misguided and wrong. Second to argue that non-oromos who live in oromia will not have any say on the issue of oromia is stupid. you brought the Scotland referendum. do you know who voted in that referendum? this groups 1,British citizens who were resident in Scotland;2, citizens of other Commonwealth countries who were resident in Scotland;3, citizens of other European Union countries who were resident in Scotland. and Scottish people who live outside of Scotland were not allowed to vote, even those who lived in the UK. So if it ever come down to referendum it should be a decision of all Ethiopians who are resident in Oromia not just who were born from Oromo parents or whose grandmother is Oromo or any of such criteria. the referendum is about the future of the people not their past.

ማሞ said...

አንበሳ ተሰፋችን አውነትን ተናግሮ የመሸበት ማደር ይለል ነበር አባቴ። አውነትን ለመናገር ግልብና ስሜታዊ መሆን አያስፈልግም። የሰከነ ቡናና ተስፋዬ እርካታ ይሰጣሉ። የኦሮሞ መብትን ረሽኖ አፈር ማልበስ ቀርቷል። የኦሮሞ መብት እንዲሁም የአማራ ደቡብ ጋምቤላና ማንኛውም በሁለት እግሮ ቆሞ የሚሄድ ሰብኣዊ ፍጡር ብሄር ሳይሸራረፍ ሳይከለስ ሳይበረዝ ሳይደለዝ ሳይጣመም ሳይጠቀለል ሙሉበሙሉ መከበር አለበት።

Anonymous said...

You Cobra Snake! You can't achieve your target of dividing the nation! It is built through time with blood and bone of our Grand fathers. You layman please try to analyze the dynamics of ethiopian oromo politics! you never know about politics.

Anonymous said...
This comment has been removed by a blog administrator.
Unknown said...

ኢትዮጵያ ያለእኤርትራ አለች።የድሮዋ ኢትዮጵያ ያለኦሮሞ ሰለመኖራ የሚናገር ሰው እየጠፋ ነው።የኢትዮጵያ አንድነት ሲባል በመድረክ ወይም በPAFD በኩል ይመጣል ብለው ብዙ ህዝቦች ወጥተው መንገድ መንገዱን እያዩ ነው።የኢትዮጵያ አንድነት በጥቂት ህዝቦች ተጅምሮ በአጭር ጊዜ ሁሉም የሚሰባሰቡበት 120 ዓመታት የትግል ድል ከደጃችን ደርሳል።
የኦሮሞ ዘመን ገባ !!!

Unknown said...

አቶ ተስፋዬ ሳንሱር አለ እንዴ ቤታችሁ።ከዚህ በፊት ፕ/ር መሳይ ከበደ ላይ የሰጠሁን አስተያየት የት እንደተወሰደ አላውቅም።ዛሬም የሰጠሁት አስተያየት የት እንዳለ አላውቅም።ለፊርማ ተልኮ ይሁን ???
የኦሮሞ ዘመን ገባ !!!

Anonymous said...

ምድረ ቀዳዳ ዐማራ ወሬ ብቻ ቡፋ ንፉ ይልቅ አንተና መሰሎችህ ይሄ እንደ ጀላ የቆመ ጭንቅላታችሁን አሰሩት

Tech with Estif said...

THANK YOU!!! "THE BLACK SOIL OF ADHA"