Thursday, November 24, 2016

የኤርሚያስ ለገሰ "ልቃቂት"


ኤርሚያስ ለገሰ ቀደም ሲል "የመለስ ትሩፋቶች" የሚል መፅሃፍ አስነብቦን ነበር። አሁን ደግሞ "የመለስ ልቃቂቶች" የሚል ደገመ። ሰሞኑን መፅሃፉን ጓደኞች ገዝተው ልከውልኝ በሁለት ሌሊት ጨረስኩት። ስጨርስ መገረሜን አልደብቅም። ህወሃት የተባለውን ድርጅት የማውቀው ይመስለኝ ነበር። "ልቃቂት"ን አንብቤ ከጨረስኩ በሁዋላ በፍፁም ህወሃትን ጠልቄ እንደማላውቅ ተረዳሁ። ኤርሚያስ ያለ ፍርሃት፤ ያለመደባበቅ የሚያውቀውን ለመፃፍ በመወሰኑ ሊደነቅም ሊመሰገንም ይገባዋል። ህወሃትን መኮነን ብቻ ሳይሆን ከነርሱ ጋር በነበረው የስራ ዘመን ለርሱ የተደረገለትን ማባበያ ጭምር በግልፅነት ፅፏል።


በዊንጌት አምሳል በመምህር አስረስ ተሰማ ስለተቋቋመው "ቀላሚኖ" ስለተባለው ትምህርት ቤት በዝርዝር የማወቅ ፍላጎት ነበረኝ። ኤርሚያስ ደህና መረጃ ሰጥቶናል። ኤፈርት ስለተባለው የወያኔ ድርጅት ፅዮን ዘማርያም አንዳንድ ነገሮችን ስታስነብበን ቆይታ ነበር። "ልቃቂት" ግን ብትን አድርጎ ከውስጥ አሳይቶናል።

የኤርሜያስ አዲስ መፅሃፍ በጣም ብዙ አስቂኝ ነገሮች አሉት። የአዜብ መስፍንን ባህርይ የገለፀበት ያስደምማል። ዑቅባይ በርሄ ሲታሰር በጣም ተገርሜ ነበር። መፅሃፉን ሳነብ ምክንያቱ ግልፅ ሆነልኝ። ማእድን ሚኒስትር የነበረው አለማየሁ ተገኑ ከኮሜዲያን አንዱ ሆኖ ቀርቧል። "በእየሱስ ስም" እያለ የሚወረውራቸው አሳቦች ደግ ናቸው። ወዳጄ በረከት ስምኦን እንደ ማርያም ጠላት ተወግሯል። ድሮ ከማውቀው በረከት የተለየ ነገር ያገኘሁት የስድብ ችሎታው መጨመሩ ነው። በተለይ "ኪራይ ሰብሳቢ" የሚለው ስድብ አሰስቆኛል። አሰፋ ጫቦ እንዳለው ወያኔ ቃላት አያልቅበትም።

ኤርሚያስ በመፅሃፉ በበአባቱ በኩል የጌጃ (ገጃ) ኦሮሞ፤ በእናቱ በኩል የሸዋ አማራ መሆኑን ነግሮን ሲያበቃ፤ እሱ አዲስአበቤ ኢትዮጵያዊ መሆኑን አስረድቶናል። ከወያኔ ጋር በነበረ ጊዜ ግን ኦሮሞ ሆኖ ኦፒዶ ውስጥ ነበር የታቀፈው። ስለ አባቱ ዘመዶች ጥቂት ነካ ነካ አድርጓል። ጌጃዎች (ገጃዎች) ሃይለኛና አአመፀኞች መሆናቸውን ጠቆም አድርጓል። የገጃ ጎሳ ጠባይ ራሱን የቻለ መፅሃፍ ይወጣዋል። አንድም ጊዜ ለመንግሰት ገብሮ የማያውቅ ህዝብ ነው። መንግስቱ ቴክሱ እንኳ አይቶ እንዳላየ ነበር የተዋቸው። ከገጃ ቀጥሎ በሃይለኛነታቸው እነ ጉጂ፣ እነ ቦረና፣ እነ ጂሌ ይታወቃሉ። አምቦ አካባቢም እምቢ ባይ ነው። አፍንጫውን አያስነካም። የእነ ሩንዳሳ አሼቴ፣ የነመረራ ጉዲና አገር አመፅ እርሻቸው ነው።


 ዞረም ቀረ "ልቃቂት" በመረጃ የተሞላ መፅሃፍ ብቻ ሳይሆን መዝናኛም ነው። በቅርፁ ላይ ግን ጉድለት አለው። 568 ገፆች ይዟል። በመስመሮች መካከል ያለውን ክፍተት አጥብቦ መደበኛ ቢያደርገው መፅሃፉ በ400 ገፅ ይጠናቀቅ ነበር። ይህም ማሳተሚያ ዋጋውን በቀነሰ። የመሸጫ ዋጋውም እንዲሁ በወረደ ነበር። እስኪ ጊዜ ካገኘሁ የመፅሃፍ ግምገማ እሰራበታለሁ።     

5 comments:

Anonymous said...

መጽሐፉን ገዝቶ ለማንበብ ከቋመጡት መካከል አንዱ ነኝ፡፡ የአንተ አፍ ያቆለጳጰሰው ነገር በአግርጥም ብዙ ቁብ ነገር ይኖረዋል ብዬ እገምታለሁ፡፡ በእርግጥ የዚያን ሰላቢ ትሩፋት አንብቤ የኤርምያስን የመጻፍ ችሎታ ከመረጃው ጋር አጣጥሜ አድንቄ ነበር፡፡ እስኪ በነካ እጅህ ይዘቱንም ዳሰስ አድርገውና እንቋደሳ፡፡ ግምገማ እንዳልል፤ የአራዳ ልጆች ግም ገማ እያሉ ቃሉን አሸተቱት፤ እንድሜ ለወያኔ፤ አርሱ ገምቶ ቋንቋን የሚያገማ ግማታም፡፡

ተስፋዬ ነኝ

Anonymous said...

Ermias wrote 2 books what about you? We're expecting something soon. Please write something your blog well known and ur short articles are so good.
Please tesfish

Ababoraa said...

Dear Tesfaye I read your comment about Ermiyas book, one thing to remind you on your note about Ambo. You called Rundasa's and Marara's (farm of rebellious). Yes they are from Ambo but the true rebellious was Argaw Dinqa the first Ambo hero arm struggle igniter during Derg Regime. To be honest you better dig the real history about Ambo. Let say the best example I heard Argaw Dinqa during Durg he was one of collected petition saying that was are not accept any Awrajaa Administrator with out local born person because we have a lot educated person do not send us any Amhara person he said. So because of that the first Awrajaa Administrator Kumsisa Lata nominated assigned.
There are so many things about Argaw Dinqa and Ambo.
Thank you obbo Gada for take a time and reading my comment.

Anonymous said...

Let us know if u no longer add new articles on your blog. This is like a drug addiction for your followers to read something new from you. Please say something.

Zozo said...

The book is amazing and everybody should read it...u can see clearly the true color of woyane...