"የኑረነቢ ማህደር" የተባለው አዲሱ መጽሃፌ ከሚተርካቸው ጉዳዮች አንዱ የአስመራን አመሰራረት ነው። በዚያን ዘመን አስመራን ለመገንባት የኤርትራውያን ጉልበት ባለመብቃቱ፣ የጉልበት ሰራተኞች ከሱዳን፣ ከየመን፣ ከአቢሲንያ፣ ከሶርያና ከኢጣልያ በሺህዎች መጥተው ነበር። አስመራን ሲገነቡ ህይወታቸው ያለፈ ቁጥር ስፍር የላቸውም። አስመራ ለዚህ ክብር መብቃትዋ ይገባታል። ዩኔስኮ ስላሳለፈው ውሳኔ የበለጠ ለማወቅ የኤልያስ አማረን ግድግዳ ይጎበኙ። Elias Amare
ሎሬት ጸጋዬ ገብረመድህን "እሳት ወይ አበባ" በተባለ የስነግጥም መድበሉ ስለ አስመራ ውበት የቁዋጠረው መወድስ እንዲህ የሚል ነበር፥
ሎሬት ጸጋዬ ገብረመድህን "እሳት ወይ አበባ" በተባለ የስነግጥም መድበሉ ስለ አስመራ ውበት የቁዋጠረው መወድስ እንዲህ የሚል ነበር፥
ምነው ሁሉ እንዳንቺ አስመራ
እንደ ከተሞች መዲና አቀያየሱ ቢጠራ
የአውራ ጎዳናሽ ጠለላ፣ ሁሉን ባክናፉ እየጠራ
አስር ሰአት ላይ ሲደራ
ለመንገደኛሽ መዝናኛ፣ ሲያጠላ፣ ሲያብብ፣ ሲያፈራ
ምነው ሁሉ እንዳንቺ አስመራ
አደባባይ ሲያነጥፉ
አድባራትና መስጊዱን፣ ካቴድራሉን በየረድፉ
ገበያውን በየመልኩ፣ እንደ አውታር እያሰለፉ
በወግ እየደረደሩ፣
በስምረት እያሰመሩ
በውበት እያዳብሩ
እያሳመሩ ቢያደሩ
በየክፍሉ፣ በየበሩ፣ በየመልኩ፣ በየተራ
ፋኖሱን እንደ ደመራ
ቡና ቤቱን እንድ ሶራ
ምነው ሁሉ እንዳንቺ አስመራ
እንደ ከተሞች መዲና አቀያየሱ ቢጠራ
እንደ ከተሞች መዲና አቀያየሱ ቢጠራ
የአውራ ጎዳናሽ ጠለላ፣ ሁሉን ባክናፉ እየጠራ
አስር ሰአት ላይ ሲደራ
ለመንገደኛሽ መዝናኛ፣ ሲያጠላ፣ ሲያብብ፣ ሲያፈራ
ምነው ሁሉ እንዳንቺ አስመራ
አደባባይ ሲያነጥፉ
አድባራትና መስጊዱን፣ ካቴድራሉን በየረድፉ
ገበያውን በየመልኩ፣ እንደ አውታር እያሰለፉ
በወግ እየደረደሩ፣
በስምረት እያሰመሩ
በውበት እያዳብሩ
እያሳመሩ ቢያደሩ
በየክፍሉ፣ በየበሩ፣ በየመልኩ፣ በየተራ
ፋኖሱን እንደ ደመራ
ቡና ቤቱን እንድ ሶራ
ምነው ሁሉ እንዳንቺ አስመራ
እንደ ከተሞች መዲና አቀያየሱ ቢጠራ
No comments:
Post a Comment