የካሊፎርኒያ ቆይታዬ በመጪው ማክሰኞ ይጠናቀቃል። ትናንት በኦሬንጅ ካውንቲ ጥሩ ቆይታ ነበረኝ። ዛሬ እሁድ ሎሰአንጀሊስ ላይ የውይይትና መጽሃፍ ላይ የመፈረም ስራ ይኖረኛል፡፡ ማክሰኞ በአወቶብስ ወደ ላስቬጋስ አቀናለሁ።
በዚህ ወር መጨረሻ የOSA ኮንፈረንስ ላይ ተሳትፌ ሳብቃ, ዳግም ወደ ሚኒሶታ እጉዋዛለሁ፡፡ ከ30ሺህ በላይ ኦሮሞዎች የሚገኙበት የስፖርት በአል ላይ መገኘት ያጉዋጉዋል፡፡ የኦሮሚያ ባንዴራ ጨረቃ መስሎ ሲውለበለብ ማየት ምን ያህል ልብ እንደሚነካ ለመረዳት የግድ ኦሮሞ መሆን ያስፈልጋል። ከሚኒሶታ ቀጥሎ ጉዞዬ ወደ አትላንታ ነው። የእውሮፕላን ትኬት ከወዲሁ ደርሶኛል፡፡
በመቀጠል ወደ ሲያትል አቀናለሁ፡፡ ቀናተኛ አድቃቂዎቼ በግንቦት ወር ሲያትል መግባቴን ቀደም ብለው የጻፉት እውነት አይደለም። ገና ልሄድ ነው። ከብዙ አመታት በፊት በዚህች ወብ ከተማ አሳ ማሸጊያ ፋብሪካ ውስጥ ወዛደር ሆኜ ሰርቻለሁ። ይኽው አሁን ዳግም ላያት ነው። ከሲያትል ቀጥሎ ወደ ቶሮንቶ ብቅ የማለት አሳብ አለኝ። ገና አልተረጋገጠም፡፡ የመጨረሻው ጉዞዬ ግን ሞስኮ ነው። ሞስኮ መሄዴ ካልቀረ ጎርኪይ የተወለደባትን ኒዥኒይ ኖቭጎሮድ, እንዲሁም ቮልጋ ወንዝን ማየት አለብኝ። በቅድመአያቱ በኩል የስጋ ዘመዴ ለሆነው ፑሽኪንም አበባ አኖርለታለሁ። ሩስያን የመጎብኘት አሳብ የነበረኝ ከአምስት አመታት በፊት ነበር። ሳይሳካልኝ ቆይቶ አሁን ግን ጊዜው ደረሰ።
ሰሞኑን ዜናዎችን ስፈታትሽ የኦሮሚያን በተለይ የአምቦን ቁጣ ሰማሁ፡፡ የወያኔ አድናቂዎች “መጣሁ!” እያሉ ላሽ ማለት ከጀመሩ ሰነባብተዋል። ሽምጥ እየጋለበ የሚመጣውን የኦሮሞ ህዝብ አብዮት ማቆም እንደማይቻል ከወዲሁ ለማወቅ ጠንቁዋይ መሆን አያስፈልግም። ሌላው ወሬ የእምቦጭ ጉዳይ ነው። ይህ አረም የጣና ሃይቅን ስለ መውረሩ የከረመ ዜና ቢሆንም ትልቅ ጉዳይ ሆኑዋል። ወያኔ እና እንቦጭ ተመሳሳይ ጠባይ እንዳላቸውም አነበብኩ። እመለስበታልሁ።
1 comment:
THANK YOU !!! "THE BLACK SOIL OF ADHA"
Post a Comment