ከድሬዳዋ ተነስተው ኤርትራ ቀይ ባህር ዳርቻያረፉት የኢትዮጵያ ሄሊኮፕተሮች ጉዳይ
ለወያኔ ራስ ምታት ሆኖበት ሰንብቶአል። ሄሊኮፕተር ይዘው ኤርትራ የገቡት ኢትዮጵያውያን የአየር ሃይል አብራሪዎች
ማንነት እና በወያኔ ላይ ያላቸው ተቃውሞ ምን እንደሆነ ገና አልታወቀም። በተያያዘ የኢትዮጵያ አየር ሃይል
ከማንኛውም ጊዜ በከፋ ሁኔታ ሽባ መሆኑን መረጃዎች ይጠቁማሉ። አማራ እና ኦሮሞ የጦር አይሮፕላን አብራሪዎች ከስራ
ውጭ ተደርገዋል። የትግራይ አብራሪዎችና ቴክኒሻኖች ደ’ሞ በጣት የሚቆጠሩ በመሆናቸው አየር ሃይልን በትግራይ ሰዎች
ብቻ ለማንቀሳቀስ አልተቻለም። በተለይም ክኒሻኖች በአብዛኛው አማራና ኦሮሞዎች በመሆናቸው ወያኔ ችግር ውስጥ
ወድቆአል። የፌክ ፌደራሊዝም ውጤት ይኸው ነው።
ከቀጣዩ ምርጫ ጋር በተያያዘ ወያኔ ብዙ ፈተናዎች ከፊቱ ተደቅነውበታል። ህወሃትና ብአዴን የስልጣን ሽኩቻ ላይ መሆናቸው ሰሙነኛ ወግ ነበር። ኦህዴድ ከጨዋታ ውጭ ሆኖአል። ድቡብ ህዝቦች፤ አልነበሩም - የሉምም። ኦህዴድን ያልያዘ የኢህአዴግንሊቀመንበርነት (ጠቅላይ ሚኒስትርነትን ጭምር) መያዝ እንደማይችል ግልፅ ነው።ስለዚህ ህወሃትና ብአዴን የኦህዴድ አባላትን በግለሰብ ደረጃ በመቀራመት የራሳቸው ለማድረግ ውስጥ ውስጡን ይሻኮቱ ይዘዋል። ኦህዴድ ለራሱ እንዳያስብ ተደርጎ ስለተሽመደመደ ከፊቱ የተደቀነው ጥያቄ፣ “ማንን ላንግስ?” የሚለው ብቻሆኖአል። ርግጥ ነው፤ የኦህዴድ አባላትን በቅርብ እንደማውቃቸው አማራ ወደ ስልጣን ከሚመጣ ህወሃት ስልጣን ላይ ቢቆይ ይመርጣሉ። ግን ደግሞ በዚህ ወቅት የአካባቢያችን ዋነኛ ጠላት ወያኔ እንጂ የአማራ ፖቲከኞች እንዳልሆኑ የሚያጡት አይመስለኝም። ወያኔ ቢወድቅ ደመራው ወዴት እንደሚወድቅ አለመታወቁ ለማናቸውም ቢሆን አሳሳቢ ነው። ሁኔታዎች ተወሳስበዋል።የኦህዴድ አመራር መግባባት ችሎ ቢደራጅ ህወሃትና ብአዴንላይ ተፅእኖ ማድረግ ይቻለው ነበር። ለአብነት ከኢህአዴግ አባል ድርጅትነት ቢወጡ ጠንካራ ተደራዳሪ መሆን በቻሉ። ከፓርላማው ራሳቸውን ቢያገልሉ ወያኔ የኦሮሞን ህዝብ ማክበር በጀመረ ነበር። በርግጥ እንዲህ ያለ ወግ፣ “እንጀራ የለም እንጂ - ወጥ ቢኖር ኖሮ” እንዲሉ ሊሆን ይችላል።
የወያኔ አመራር አባላትም መስቀለኛ መንገድ ላይ ናቸው። አማራ ወደ ስልጣን ከሚመጣ ኢትዮጵያ ብትፈራርስ እንደሚመርጡ ግልፅ ነው።የአቦይ ስብሃት ነባር አቋምይታወቃል። ሃይለማርያምና ደመቀ (አገውና ወላይታ - ፕሮቴስታንትና ሙስሊም) ወደ ስልጣን ሲመጡ፣ “የኢትዮጵያን ስልጣን ከአማራና ከኦርቶዶክስ አፅድተነዋል” ብሎ በሬድዮ ሲናገርተሰምቶአል። ለነገሩ የተሳሳተ አይመስለኝም። ኮሎኔል መንግስቱ በማፈራረስ የጀመረውን የኦርቶ - አማራ ቢሮክራሲ ወያኔ በተሳካ ሁኔታ አጠናቆታል። ስለዚህ ብአዴን (አማራ ነው ከተባለ) የፈለገውን ያህል ቢፍጨረጨር የጋረዳለቲን በተመንግስት እንዲቆጣጠር ሌሎች አይፈቅዱለትም። ህወሃት ደብረፅዮንን ወደ ጠቅላይ ሚኒስትርነት ሊያመጣ ማሰቡ ሲናፈስ የሰነበተው ወሬ ልክ አይመስለኝም። ደብረፅዮን የቴክኒክ ሰው ነው። የኢትዮጵያን ፖለቲካ ለማሽከርከር የሚቻለው ፖለቲከኛ አይደለም። በዚህ ወቅት ህወሃት ወደ ስልጣን ሊያመጣው የሚችለው ብቸኛ ተቀባይነት ያለው ሰው ቢኖር ቴዎድሮስ ነው። ትውልዱ ከአድዋ የሚመዘዘውን፣ አስመራ ተወልዶ ማደጉ የሚነገርለትን ቴዎድሮስ አድሃኖምን በመለስ ዜናዊ ወንበር ላይ ማስቀመጥም ቢሆን ግን ለህወሃት አስቸጋሪ ነው። ቴዎድሮስ አድሃኖም የሚናከስ ጥርስ የለውም ተብሎ ይታማል። ኢትዮጵያን ለመምራት ደግሞ የሚናከስ ብቻ ሳይሆን፣ የሚቦጭቅና የሚያኝክ ጥርስ ያስፈልጋል። ህወሃት ቴዎድሮስ አድሃኖምን ወደ ስልጣን ማምጣት ይመኙ ይሆናል። ቴዎድሮስ ስልጣኑን ቢይዝ ለህወሃት ጥቅም ነው። አደገኛ ጉዳትም ግን አለው። ጫጫታውን አይችሉትም። ከውስጥም ከውጭም የሚወረወርባቸውን የተቃውሞ ፕሮፓጋንዳ መሸከም ስለመቻላቸው ርግጠኛ አይደሉም። ስለዚህ ሃይለማርያምን ወይም እሱን የመሰለ ታዛዥ ሰው እየለዋወጡ፣ ከጀርባ እየተቆጣጠሩ ድምፃቸውን አጥፍተው ስልጣን ላይ መቆየቱን ይመርጡ ይሆናል።
ሃይለማርያም በህወሃትና በብአዴን ተከቦ ስራውን ሲሰራ ሰንብቶአል። መከላከያ፣ ደህንነትና ውጭ ጉዳይን ማዘዝ አይችልም። መንግስትን መንግስት ሊያሰኙ የሚችሉት እነዚህ ሶስቱ ቁልፍ ቦታዎች ደግሞ በህወሃት የተያዙ ናቸው። በጌታቸው አሰፋ፣ በሳሞራ የኑስ እና በቴዎድሮስ አድሃኖም መዳፍ ስር ናቸው። ስለዚህ ሃይሌ ቴክሱ ስልጣን አልባ ሆኖ (በጌታ ፈቃድ) የታዘዘውን ሲሰራ ቆይቶአል። ያም ሆኖ ሃይለማርያም በተቀረው የአስተዳደር ቦታ የተቻለውን ያህል የደቡብ ሰዎችን ለመሰግሰግ መሞከሩ አልቀረም። ይህ ሁኔታ እንግዲህ ለረጅም ጊዜ በአማራ ተይዞ የቆየውን የማእከላዊ መንግስት የአስተደዳር ቦታዎች እያዳከመ ስለሚሄድ፣ የአዲሳባን ቢሮክራሲ የሰው ሃይል ሚዛን ስለሚያመጣጥነው ወያኔዎችም አይጠሉትም። ከዚህ ባለፈ ሃይለማርያም ሊያደርግ የሚችለው የለም። “ሃይሌ ጥርስ አብቅሎ እነ አባይ ፀሃዬን አልታዘዝም ማለት ጀምሮአል” የሚለውን ሹክሹክታ ለጊዜው ለማመን እቸገራለሁ። መጠበቅ ይሻላል።
ኦቦ ሌንጮ ለታ ለቀጣዩ ምርጫ ወደ ፊንፊኔ ያቀናል ሲባል ተሰንብቶ ነበር። እምን እንደደረሰ አልተከታተልኩትም። ሌንጮ ጠቅልሎ ቢገባ ግን ወያኔ የሚጎዳ እንጂ የሚጠቀም አይመስለኝም። እንኳን ሌንጮ ገብቶ መረራ ጉዲና እንኳ እያዋዛ ፈተና ውስጥ ጨምሯቸዋል። በቀጣዩ ምርጫ በመጠኑም ቢሆን ወያኔን ሊፈታተን የሚችለው መረራ ጉዲና ነው። ስልጣን ይገለብጣል ተብሎ ባይታመንም ጥቂት የፓርላማ ወንበሮችን ያገኝ ይሆናል። ሌንጮ ተሳክቶለት ፊንፊኔ ገብቶ አስማተኛውን የኦነግ ባንዴራ ማውለብለብ ቢችል የምርጫ ሜዳውን ሞቅ ደመቅ ባደረገው። ወያኔም ቢጫ ወባ በሽታው በተቀሰቀሰበት ነበር። በነገራችን ላይ “ODF” የሚለው ምህፃረ ቃል Oromia Defence Force መስሎ ይሰማኛል።
አሜሪካኖች ህወሃትን እየደገፉ መሆኑ አይካድም። ህወሃትም ቢሆን ለአሜሪካ ብብቱን ከፍቶ ሰጥቶአቸዋል። አሜሪካኖች በህወሃት አመራር ባገኙት ጥቅም ደስተኛ ቢሆኑም፤የወያኔ ስርአት በስልጣን እንዲቆይ ይፈልጋሉ ማለት ግን አይደለም። “አናሳ ብሄረሰብ በስልጣን ላይ ሊቆይ ከሚችለው በላይ ገዝታችሁዋል። ከዚህ በላይ መሄድ አትችሉም። ችግር ሳይገጥማችሁ ቦታውን ብትለቁ ይሻላል።” ብለው ደጋግመው መክረዋቸዋል። ወያኔ የህዝብ ድጋፍ ስለሌለው አገሪቱን ገፍቶ ገፍቶ ገደል ይጨምራታል ብለው ሊሰጉ ይችላሉ። አሜሪካኖች እንደ ሰማያዊ ፓርቲ ያሉትን ከጀርባ ደጋግፈው ወደ ስልጣን ለማምጣት እንደሚፈልጉ ይታወቃል። ስለ ኦሮምያ ነፃነት የሚያስቡ ወጣቶችን ግን አሜሪካኖች በጣም ይፈሯቸዋል። “በኢትዮጵያ አንድነት” የሚያምን፣ በኦሮሞ ህዝብ ዘንድ ተቀባይነት ሊኖረው የሚችል ወጣት ኦሮሞ ለማግኘት መከራቸውን ሲያዩ ሰንብተዋል ይባላል። የሚሳካላቸው አይደለም። በርግጥ በመጪው ዘመን የኦሮሞን ህዝብ በትክክል የሚወክል ሃይል ወደ ስልጣን ካልመጣ የኢትዮጵያ አንድነት አደጋ ላይ እንደሚወድቅ ምእራባውያኑ አስጠንተው ደርሰውበታል። ያም ሆኖ ኦሮሞዎች ካላቸው አቅም አንድ አስረኛውን እንኳ እንዳልተጠቀሙ ይታመናል።
የአንድነት ሃይሎች የፖለቲካ አካሄድ ቀልድ ይመስለኛል። አንዳርጋቸው ፅጌ፣ “ነፃነትን የማያውቅ ነፃአውጪ” ብሎ ነበር። “አንድነትን የማያውቁ አንድነቶች” ከፕሮፓጋንዳ ባሻገር የትም መሄድ አልቻሉም። ኢትዮጵያዊነት ባለቤት አጥቶአል። ህይወቱን ቀርቶ እንቅልፉን የሚሰዋለት እያጣ ነው።ጠጋ ብሎ ላያቸው “አንድነቶች” በጎንደርና በጎጃም፤ በወሎና በመንዝ ተከፋፍለው ሲሻኮቱ ይገኛሉ። የጎንደር - ሸዋ ሽኩቻቸውን ሳይፈቱ ኦጋዴን ኢትዮጵያዊነትን እንዲዘምር ይመኛሉ። ብዙውን ጊዜ የአማራ ፖለቲከኞች፣ “ኦሮሞ ወንድሞቻችን” ማለት ያበዛሉ። በአማራ ፖለቲከኞች ዘንድ፣ “ግማሽ ኦሮሞ ነኝ” ማለት ፋሽን ሆኖአል። በአንፃሩ የኦሮሞ ፖለቲከኞች፣ “አማራወንድሞቻችን” የሚል አባባል ሲጠቀሙ ሰምቼ አላውቅም። አንደኛው ተለማማጭ የመሰለበት ምክንያቱ ምንድነው? ከልብ ስላልሆነ ይመስለኛል። “ወንድሞቻችን” የሚለው አባባል የለበጣ ነው።የኦሮሞን ህዝብ ስነልቦና “የቡርቃ ዝምታ” በተባለው መፅሃፌ ጥሩ አድርጌ በመግለፄ እኔ የአማራ ህዝብ ባለውለታ እንደሆንኩ ይሰማኛል። አሁንም አማራ ፖለቲከኛ ወንድሞቼን በግልፅ መምከር እፈልጋለሁ። ጊዜ እያመለጠ ነው። የአማራ ፖለቲከኞች ከሽማግሌ ኦሮሞዎች ጋር ዛሬውኑ ተግባብተው ለመስራት ካልሞከሩ በርግጥም ጊዜ እያመለጣቸው ነው። ሽማግሌዎቹ ቢያንስ በኢትዮጵያዊነት ስር ኖረዋል። ወደውም ሆነ ተገደው ለባንዴራው ዘምረዋል። አዲሱ የኦሮሞ ትውልድ ግን አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ቀለሙን ባንዴራ አጥብቆ ይጠላዋል። አማርኛን ይጠየፋል። ‘ኢትዮጵያዊ ነኝ’ ማለት አይፈልግም። የአንድነት ሃይሎች ዛሬውኑ መባነን አለባቸው። ዮሃንስ መጥምቁ፣ “ከኔ በሁዋላ የሚመጣው በእሳት ያጠምቃችሁዋል!” እንዳለው እየመጣ ያለው የኦሮሚያ አዲሱ ትውልድ ከአበሻ ጋር ቁጭ ብሎ መነጋገር ስለመቻሉ እጠራጠራለሁ። መልካም አዲስ አመት፤ መልካም የገና በአል ይሁንልን። አላህ ይርዳን። አሜን!
Gadaa Ghebreab, የቅዳሜማስታወሻ፣ Dec 27 2014 Email: ttgebreab@gmail .com

Gadaa Ghebreab, የቅዳሜማስታወሻ፣ Dec 27 2014 Email: ttgebreab@gmail
5 comments:
You are absolutely right Tesfish. But as you know that Ethiopian politics always lack discussion and compromise. Especially, those pro-unity groups have no convincing and timely political strategies to sale their ideas except promoting the flag and celebrating good old past even sometimes with no provision of any tangible evidence for some of their arguments plus insulting people with different opinions. In others words, they lack courage to discuss on the real facts on the ground and on wrong doings in the pasts. We missed Eritrea because of this political ignorance of the so called ex-leaders as well as there is no guarantee about the continuity of the unity of the country under the prevailing realities on the ground. Unity is, of course, a very good notion but needs extra cares, trust and compromise.
So my advice to Ethiopian elites, particularly to pro-unity elites, is "be courage to carefully observe what are going on in Ethiopian politics and try to at least listen to those with different opinions and based on that design convincing political strategy that can build trust and unity among all parties"
I don't have a word to express how pleased I am on the way you put the facts. Please keep it up. By the way I have seen different books of 1930-1980s written by norwegian journalists. There are a lot of books on Ethiopia and Eritrea. Unfortunately the books are written in norwegian and only available with norwegian IP. Otherwise it is free and anyone can read on line.For your information : www.nb.no
This is just your pure imagination. That'w what we call the Politics-fiction.
hulum ETHIOPIAWI ende zega tekababro, yeminorbat Ethiopian kalfetern.Lets be ready to creat Oromia, somalia, and so.
Fikir yachenfal.
ቅዠትህን በማንበቤ ተዝናንቻለሁ።
እባብ ያሉህ ሰዎች እውነታቸውን ነው።
Post a Comment