Friday, January 30, 2015

የኦሮሚያ ደራስያን ማህበር (OWA)

በውጭ አገር የሚገኙ መፅሃፍ ያሳተሙ ኦሮሞዎች OWA (Oromia writers Association) ለማቋቋም በዝግጅት ላይ መሆናቸውን ሰሞኑን ወሬ ሰማሁ። አሳቡን አልጠላሁትም። በርግጥ “የአፍሪቃ ቀንድ ደራስያን ማህበር” ቢሆን ይመረጥ ነበር። ትልቁ ጃንጥላ እስኪዘረጋ አነስተኛዎቹን መጠቀም ግን ክፋት የለውም። የኢትዮጵያ ደራስያን ማህበር የአማርኛ ፀሃፊዎችን ብቻ የሚያገለግልና የሚያበረታታ በመሆኑ የOWA መቋቋም አስፈላጊነቱ አያጠያይቅም። እዚህ ላይ ግን በጥብቅ ማንሳት የምፈልገው አሳብ አለ። ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን እና ደራሲና ጋዜጠኛ በአሉ ግርማ እንደ ቀዳሚ የኦሮሚያ ፀሃፊዎች መጠን ስማቸውና ስራቸው በማህበሩ መመስረቻ ፅሁፍ መካተት ይኖርበታል።
ፀጋዬና በአሉ ጊዜው በሚፈቅድላቸው መጠን ለኦሮሞ ህዝብ አርነት በብእራቸው ታግለዋል።በቀጭን መስመርም ቢሆን መልእክታቸውን ለማስተላለፍ ሞክረዋል። ባለቅኔ ፀጋዬ ገብረመድህን “አዋሽ” በሚል ርእስ የፃፈው ግጥም ለኦሮሞ ህዝብ አርነት ታጋዮች መሆኑ ይታመናል። የአዋሽን ግጥም መታሰቢያነት ለጋማቹ ቃማሊቲ ነበር የሰጠው። አበሾች “ጋማቹ” ማለት ስለማይችሉ “ገመቹ” ይላሉ። “ቃማሊቲ” ቃሉ ኦሮምኛ ሲሆን፣ ትርጉሙ “ጦጣው” ማለት ነው። ጋማቹ ማን እንደሆነ ፀጋዬ አልነገረንም። ምናልባት እንደ አብሼ ገርባ ወይም እንደ አገሪ ቱሉ የአርነት ትግል ጀምሮ በአጭሩ የተቀጨ ታጋይ ሳይሆን አይቀርም። ጋማቹ ቃማሊቲ ማን እንደሆነ ለማወቅ ብዙ አጠያይቄ ሳይሳካልኝ ቀርቶአል።

የሎሬት ፀጋዬን የ”አዋሽ” መልእክት በትክክል ለመረዳት “አዋሽ” የሚለውን ቃል “ኦሮሞ” በሚል በመተካት መረዳትን ይጠይቃል። የቀዌሳ የልጅ ልጅ ፀጋዬ የኦሮሞን ህዝብ የነፃነት ጥያቄ በቅኔዎቹ ያንጎራጎረ የመጀመሪያው የአማርኛ ቋንቋ ባለቅኔ ነው። በመቀጠል የኦሮሞን ህዝብ የአርነት ጥያቄ የነካካው ዝነኛው ደራሲ በአሉ ግርማ ነበር። በአሉ ግርማ “ካድማስ ባሻገር” በሚለው መፅሃፉ እና “ኦሮማይ” ላይ ሁለት ገፀባህርያትን በመሳል የኦሮሞን ህዝብ ጥያቄ አንስቶአል። በአሉ ግርማ “ካድማስ ባሻገር” በተባለ መፅሃፉ ጫልቱ የተባለች ዋና ገፀባህሪ አስተዋውቆናል። ስሟን ሉሊት ታደሰ ብላ ቀይራ ትታያለች። ሞታ በተቀበረችው በቀድሞይቱ የኢትዮጵያ ኤምፓየር ውስጥ፣ “ጫልቱ” በሚል ስም መኖር ስለማይቻል ስሟን መቀየሯን አበራ ለተባለ ጓደኛዋ በምስጢር ታጫውተዋለች። ያም ሆኖ መፅሃፉ ሲያልቅ አበራና ሉሊት ጋብቻ ለመፈፀም አይበቁም። አበራ ወርቁ እስርቤት ገባ። “ጫልቱ እንደ ሉሊት” ህይወቷን ቀጠለች። በአሉ ግርማ በመቀጠል፣“ኦሮማይ” ላይ ታደሰ ቆሪቾ የተባለ ገፀባህርይ ይዞ መጣ። ሉሊት (ጫልቱ) የአባቷ ስም ታደሰ ነበር። የኦሮማይ ገፀባህርይ ታደሰ ቆሪቾ (የሉሊት አባት?) OLF ሆኖ መጣ። የቆሪቾ ወንድ ልጅ ከደርግ የመሳሪያ ግምጃ ቤት ጠመንጃና ሽጉጦችን“ለጠላት” የማሸጋገር ስራ ይሰራ ነበር። “ታደሰ ቆሪቾ መሳሪያ ያሸጋገረው ለማነው?” የሚል ጥያቄ የግድ ይነሳል። ለOLF ካልሆነ ለማን ሊሆን ይችላል?

ሎሬት ፀጋዬ በወቅቱየኦሮሞን ህዝብ የአርነት ጥያቄ በቅኔ ለመግለፅ እንደሞከረ ይሰማኛል። “እሳት ወይ አበባ” በሚል ርእስ በታተመው ጥልቅ ባህር በሆነው የስነግጥም መድበሉ ውስጥ ፀጋዬ፣ “አዋሽ” ሲል የገለፀው የኦሮሞን ህዝብ ትግል ይመስላል። ፀጋዬ በድምፁ “አዋሽ”ን ባነበበ ጊዜም አዋሽ እንደ ሩስያው ዶን፣ እንደ እንግሊዙ ቴምስ ወንዞች የህዝብ ምሳሌ መሆኑን በአንደበቱ ተናግሮአል። ዞረም ቀረ ተደራስያን ጥበባዊ መፃህፍትን በራሳቸው መንገድ የመረዳት መብት ያላቸው እንደመሆኑ “አዋሽ” ለኔ እንደ ገባኝ ያህል አቅርቤዋለሁ።

አዋሽ ወንዝሕዝብን ወክሎ እንደተፃፈ ፀጋዬ ደጋግሞ ገልፆአል። ግጥሙ የተፃፈው በግእዝ አቆጣጠር 1964 መሆኑሲታሰብ፣ የአዋሽ ገፀባህርያት ኦሮሞዎች መሆናቸው ሲመዘን፣ ፀጋዬከመጫና ቱለማ ማህበር ምስረታ ጋር አስታኮ አዋሽን እንደፃፈ ማሽተት እንችላለን። እንዲህ ይላል ሎሬት ፀጋዬ፣

አዋሽ ቡርቃው - መጫ ምንጩ
ዳዳ ፅንሱ፣ ሸዋ ፍንጩ
የንዳዱ የበረሃ እጩ
አዋሽ የመጫ ስር ፍሳሽ
የዳዳ የቱለማ ደም
በረሃ እምትደመደም?

መጫ ቋጥሮ፣ ሸዋ ፀንሶ፣ ሰባት ቤት ጉራጌ አርግዞ
ከዳዳ ምንጭ፣ አሩሲ እምብርት፣ ከነቅሪቱ ተጉዞ
ከአላባ ጣፋ ሼህ ሁሴን፣ አዳል ሞቲ ሽሉን ይዞ
ከከረዩ ማታሃራ፣ ከኢቱ እስከ አፋር አምጦ

ከዚያም ፀጋዬ አዋሽን እያሞገሰ መልሶ በምሬት ይወቅሰዋል።“አሸዋ” እና “በረሃ” እያለ የሚጠቅሰው የኦሮሞን ህዝብ አፍኖ በመበዝበዝ ላይ የነበረውን፣ በቀላድና በገባር ስርአት ጠፍንጎ በወቅቱ የኦሮሞን ህዝብ ባርያ አድርጎ በመግዛት ላይ የነበረውን የአማራ ገዢ መደብ ይመስላል። በቀጥታ አነጋገር የኦሮሞ ህዝብ ሰፊ ቁጥር ይዞ ሳለ፣ የጀግኖች መፍለቂያ ሆኖ ሳለ፣ በአናሳዎች ታፍኖ መበዝበዙን በማንሳት ፀጋዬ ምሬቱን በቅኔዎቹ ያዥጎደጉደዋል። እንዲህ እያለ፣

እስከ መቼ ይሆን አዋሽ?
አሸዋ ለአሸዋ ድኸህ
ውስጥ ለውስጥ ምሰህ ጠልቀህ

አዋሽ ዘለአለምክን ፈስሰህ ባታልቅ
ምነው ተስፋ መቁረጥ አታውቅ?

እስከ መቼ ይሆን አዋሽ?
አዋሽ በቃኝ አትል ቆራጥ
ማን ያስተማረህ ፈሊጥ ነው፣ አረህ ለማለምለም መዋጥ?
አሻቅበህ ወደ ምስራቅ፣ ወደ ጀምበር መውጫ መናጥ?

አዋሽ ቡቡ፣ ሮሮ ብርቁ
የዘልአለም ንዳድ ስንቁ
አዋሽ አባ ብቻ ጉዞ
ዘልአለም ብሶት አርግዞ

እነ ዋቤ ሸበሌማ ሰብረው ውቅያኖስ ሲዘልቁ
እነ ግዮን ወርደው አልፈው ሱዳንን ምስርን ሲያጠምቁ
ምነው ያንተ ጉዞ ብቻ በረሃ ላይ መታነቁ?

እስከ መቼ ይሆን አዋሽ፣ ወዝክን አሸዋ ሲውጥህ
ደምክን በረሃ ሲመጥህ
ዘልአለም ሲመዘምዝህ?
እስቲ አንዴ እንኳ እንደነዋቤ፣ ባክህ ሂድ ውቅያኖስ ግባ
ዘለአለም በአሸዋ ሆድ ተውጠህ ከምታነባ

ቆራጡ እንኳ አንተ ነበርክ፣ የጀግኖች መፍለቂያ ኩሬ
የሰንጋ ፈረሰኞቹ፣ የነኦርዶፋ ጨንገሬ
የስንቱ መጠጊያ ዋሻ፣ አዋሽ ደኔ አዋሽ ዱሬ
የጥንተ ፍጡራን መደብ፣የቅድመ ማልካ ካንቱሬ

የኦሮሞ ህዝብ በተለይ ከአጤ ምኒልክ ስርአት ወዲህ በነፍጠኛው ስርአት ተወሮ የደረሰበትን አፈናና በደል ፀጋዬ በግልፅ አስቀምጦታል። የኦሮሞን ህዝብ “ተገድለህ ተጨፍጭፈህ የማታልቅ፣ ተስፋ የማትቆርጥ” ብሎታል። የኦሮሞ ህዝብ በህዝብ ብዛቱና ብቃቱ ቀዳሚ ሆኖ ሳለ፣ ጥያቄውም ተገቢና እውነት ሆኖ ሳለ፣ ዘልአለም የባእዳን ተገዢ በመሆኑ ፀጋዬ ተቆጭቶ ወቅሶታል። ኦሮሞዎች የገዛ ወገናቸውን ለመጨፍጨፍ የሌሎች መሳሪያ መሆናቸውን ፀጋዬ አንስቶ ተብከንክኖአል። “መጨፍጨፉ፣ መታፈኑ አይበቃህም ወይ? በቃኝ አትልም ወይ?” ሲል የኦሮሞን ህዝብ ጠይቆታል።

አዋሽ በቃኝን አታውቅም?
በምድር ማህፀን ከአድማስ አድማስ ዘለአለምክን ስታዘግም?
ወርደህ ሟጠህ ተንጠፍጥፈህ፣ አሜን ታከተኝ አትልም?

አዋሽ ... የመጫ ቱለማ ደም ፍሳሽ...
ካገር ወዲያ ሞት ላትሞት፣ ካገር ምጥ ወዲያ ላታምጥ
እስከመቼ ይሆን አዋሽ ራስክን በራስህ እምትውጥ?

እስከ መቼ ይሆን አዋሽ - አዋሽ አባ ቡቡ ብሶት
የሰው ችግር ሳይደርስብህ፣ ሳይቸግርህ የእውነት እጦት?
ላትዘልቀው ላያዘልቅህ፣ ለማንም የትም እምትሞት?
እስከ መቼ ይሆን “ኦሮሞ?”
ወዝክን አሸዋ እሚውጥህ
ደምክን በረሃ እሚመጥህ?
አጥንትህን ምድረበዳ፣ ሃሩር እሚመዘምዝህ?

እስከ መቼ ይሆን አዋሽ?
ተስፋ መቁረጥን እማታውቅ?
ፈስሰህ ተሟጠህ እማታልቅ?

ሎሬት ፀጋዬ የኦሮሞን ህዝብ አምርሮ የወቀሰው ራሱን ከተጠያቂነት ገለል አድርጎ አልነበረም። “አቴቴ ዱብራ ኦሮሞ” በተሰኘ ግጥሙ ራሱንም አፈር ያበላዋል። ሎሬት ፀጋዬ ራሱን ከአማራው ገዢ መደብ ቤተሰብ ውስጥ ቀላቅሎ የኦሮሞን ህዝብ እንደከዳ በግልፅ ቋንቋ ነበር ያስቀመጠው። ፀጋዬ ራሱን ከአማራው ገዢ መደብ ጉያ መጨመሩን እንደ ሃጢአት ቆጥሮ “ሰይጥኛለሁ” (ሰይጣን ሆኛለሁ) ሲል ነበር የገለፀው፣

አቴቴ ዱብራ ቦረና - አቴቴ ዱብራ ኦሮሞ
ምንም ቢርቅ ምንም ቢሸሽ፣ ህልሜ ከህልምሽ ተዛሞ
በአይንሽና በአይኔ መሃል፣ የሃሰት ስልጣኔ ቆሞ
ባንተያይ ባንወያይ፣ አቴቴ ዱብራ ኦሮሞ
እንደ ልጅነት ሰመመን፣ ለካስ እድሜም ያማል ከርሞ?

አቴቴ ዱብራ ኦሮሞ፣ እጄን በትዝታሽ ያዢኝ
በህልም ጣቶችሽ ሳቢኝ
መቸም በውን አልሆንሽም፣ እንዲያው በሰመመን ዳሺኝ
የኔ እጅ እኮ እርፍ አይጨብጥም
የኔ ክንድ ተልም አይተልምም
የኔ ጣት አረም አይነቅልም
በፊደል መፈደል በቀር፣ ጉልጓሎ እኮ አይጎለጉልም
ለስልሻለሁ፣ ሰልጥኛለሁ፣ ሰይጥኛለሁ አልሆንሽም።

አቴቴ ዱብራ ቦረና
መቼም ሁሉን ቻይ ነሽና
አጥንቴ ከአጥንትሽ ማእድን፣ ቢመነጭም ተቀምሞ
ከ“ሃና” ከ“አሃዱ” በፊት ከቃል በፊት አስቀድሞ
ዛሬ በአይንሽ በአይኔ መሃል፣ አጉል ስልጣኔ ቆሞ
ሰየጠንኩና አልሆንሽ አልኩ፣ አቴቴ ዱብራ ኦሮሞ

በአሉ ግርማ እና ፀጋዬ ገብረመድህን ጊዜው በሚፈቅድላቸው መጠን የኦሮሞን ህዝብ ጥያቄ ለመነካካት መሞከራቸው ያስመሰግናቸዋል። ያቅማቸውን ያህል በመሞከራቸው እንደ ትግል ጀማሪዎቹ እንደ ባሮ ቱምሳ እና ማሞ መዘምር፣ እንደነ ጄኔራል ታደሰ ብሩና አለሙ ቂጤሳ፣ በአሉና ፀጋዬም ስማቸው ሊዘከር ይገባዋል። OWA (የኦሮሚያ ደራስያን ማህበር) ከፍተኛ ገንዘብ ተመድቦለት፣ የትርጉም ስራ ሊሰሩ የሚችሉ ወጣቶችን አሰባስቦ በሺዎች የሚቆጠሩ መፃህፍትን ወደ ኦሮምኛ ቋንቋ ያስተረጉማል፣ ያሳትማልም ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ።

Gadaa Ghebreab, www.tgindex.blogspot.com Email: ttgebreab@gmail.com january 31 2015

9 comments:

Fisagoles said...

????
Sorry!!!......

Unknown said...

ሁለቱን ገፀ-ባሕርያት ለማዛመድ ያደረከው ሙከራ ገራሚ ነው፡፡

ግን አንድ ችግር አለ፤ ባለፈው ዘመን ታደሰ የሚል ስም የወጣለት ሰው ጫልቱ ብሎ ልጁን የመሰየም አጋጣሚ ምን ያህል ነው?

አሁን አሁን ወደኦሮምኛ ስሞች የመመለስ ዝንባሌ ቢታይም ያለፈው ትውልድ ውስጥ ያ የነበረ አይመስለኝም፡፡

CHANGES said...

Hi tesfaye, how are you doing? pls. write about the sun of bushoftu i.e Debrezeit and the society around there like Adea farmers day in day out life, Zequala, , rather peoples dividing ideas with silly tribal differentiation ,bcs. when I read your books I just remember peshkov(M. Gorky) and I feel alright with full of joy except the politics (what I hate) The politics point that you raised makes you a little one in my eyes when I remember the best art of pre-bolshevik Russian writers and also that able to make you a good for nothing than worthwhile we were living here in our mother land(ethiopia and it includes midiri bahr/bahre negash/)for centuries and will live for another centuries in love and peace. today's your action is a mortal idea comparing with the giant idea of togetherness of the peoples and tribes of ethiopia and midri bahri. If you read history of people no one can change the tribes togetherness with handful writer,politician,worriers...
I am not from the three giant tribe of ethiopia i.e The Oromo, Amhara nor tigirian.. But I must care for the country that fathers died with full of pride. Thank you Sir, Goodby.

CHANGES said...
This comment has been removed by a blog administrator.
obi harara said...

Thank You Tesfish

Unknown said...

My problem is with your incredible falacies, in misusing the writers you mention in support of your argument. Unless you have a more serious argument, it is really shamful to give them such intentions.
Again, your right to support OLF. I just feel sad about your hateful words about everything ethiopian. I don't know if you write as well in Oromifa or Tigrinia as in Amharic. May be you can share your political thoughts in those language? Unless of course you are doing these on purpose... which is why I feel really sorry for you. You wrote sometime that we are from a region where people seem condamend to do anything but what they are gifted for. You are a gifted writer, you have certainly other talents too. But as a politician, you very petful. Cheers

Anonymous said...

If you talk about their Oromo half, what about their other half?
You have an identity crisis and just don't know where you fit in?
Ethiopia? Eritrea? Oromo (Clearly you are not!!!)?
Someone with such a problem could be understood but those like you who preach what they are not and don't believe in are PATHETIC at best.

Unknown said...

Yonatan Shimells, I don't understand why you just try to attack Tesfaye ( Gadaa) for what he wrote in behalf of oromo? let's put on table and find out solution, what made you upset in his article about oromo?
if you have hatred spirit of oromo...it's better to keep quiet and even hide your self from social media.
Long Live For Gadaa!!

Yonas Ye kibi said...

tnx tesf...