Wednesday, April 25, 2018

አትመንጥሩ አትመንጥሩ - ደኑን ስንላችሁ

"ለአማራ ህዝብ መብት መከበር እንታገላለን" የሚሉ ወገኖች የዶክተር አብይ አህመድን ስም ለማጠልሸት ሲተጉ አይቼ ገረመኝ። በጣም ገረመኝ። እውነት ለመናገር እሱ ራሱ የባህርዳር ስብሰባ ላይ እንዳለው ለአማሮችም ሆነ ለአንድነት ሃይሎች ከሰማይ የወረደላቸው በረከት ነበር። እጁን ብቻ ሳይሆን እግሩንም ስመው ቢቀበሉት ያዋጣቸዋል።

እነዚህ ፖለቲከኞች ኢትዮጵያዊ የነበረውን ዶክተር መረራ ጉዲና ገፍተው ገፍተው OLF -ኦሮሚያዊ አደረጉት። ዛሬ ላይ ቆም ብለን ስናየው፤ ኦቦ በቀለ፣ ዶክተር መረራ እና ኦቦ ዳውድ በአመለካከት ተቀራርበዋል። ሁኔታዎች በዚሁ ከቀጠሉ ተረኞቹ ለማና አብይ ናቸው።

እና አንድ የቆየ ግጥም ትዝ አለኝ። በመጠኑ ስትቀየር እንዲህ ትሆናለች። ትንቢት ሳይሆን ለእውነት የቀረበ...

አትመንጥሩ አትመንጥሩ - ደኑን ስንላችሁ
መረራ፡ በቀለ፡ አብይና ለማ - ኦነግ ሆኑላችሁ

ነብሩም አንበሳውም ጎሹም ሄደላችሁ

1 comment:

Anonymous said...

You need to go and take a dip at Debre Bizen. That way, you might get cure from the evil spirit you are living with. Although great to see people move freely between Asmara and Addis, that how it should have been, You are not welcome with your toxic hates.

Beal hinzi wedi teben
Nskas tirefena
Keytimestana