ባሳለፍነው የገና ፆም ሰሞን የአለሙ አጋን የበገና ዜማዎች እየሰማሁ
ስፆምና ሰጸልይ ሰንብቼ ነበር። ከዜማዎቹ ሁሉ የሚከተሉት ስንኞች ትኩረቴን ለመሳብ በቁ፣
ይበላሃላ! ይበላሃላ!
አንተንም አፈር ይበላሃላ!
እንደ ሞኝ ሰው - እንደ ተላላ
በላው አፈር...
ያንን አንድነት - ያንን ባህል - ያንን ፍቅር
በላው አፈር...
ያንን ታሪክ - ያንን ዘመን - ያንን አገር
በላው አፈር...
ያስተማረህን - ያንን ምሁር
በላው አፈር...
ያንን የዋህ ሰው - ያንን ገበሬ
በላው መረሬ...በላው መረሬ
አንተንም አፈር ይበላሃላ!
አንቺንም አፈር ይበላሻላ
እንደ ሞኝ ሰው - እንደ ተላላ
አለሙ አጋ በበገና ዜማ ያዜመው ከሃምሳ አመታት በፊት ነበር። እውነት ነው፤ ያ ዘመን፣ ያ ታሪክ፣ ያ አገር ዛሬ የት አለ?
ብለን ስንጠይቅ“አለሙ አጋ ነቢይ ነበርን?” ለማለት እንገደዳለን። ይህን በመሞነጫጨር ላይ ሳለሁ የጣይቱ ሆቴል በእሳት ሲቃጠል
በቴሌቪዥን ይታየኝ ነበር። “አፈር የበላው ቅርስ” የሚል አባባልም ወደ አእምሮዬ መጣ።
No comments:
Post a Comment