Wednesday, August 2, 2017

መረራ ጉዲና ሆይ! ትእግስት ሲሙዋጠጥ አየሁ!!

Image may contain: one or more people, people standing and outdoorእነዚህ ሰዎች እንዴት እንደሚያሰቃዩህ አየሁና ደነገጥኩ። ወገኖችህ መሳቀቃቸውንም በማህበራዊ ድረገጾች ላይ አንብቤያለሁ። ኦሮሞዎች ወይም መላ ኢትዮጵያውያን ስላንተና ሰለ በቀለ ገርባ እያነሱ በቁጭት ይነጋገሩ ነበር። በወዳጆችህ ገጽታ ላይ ወደ በቀል የሚያመራ ስሜትም አየሁ። ትእግስት ሲሙዋጠጥ በአይኔ በብረቱ፡ በጆሮዬ በጅማቱ፡ አየሁ! ሰማሁ!! ደጋፊዎችህ ማእበልና ጎርፍ ናቸው። ጊዜውም ከማእበሉ መነሳት በፊት ያለውን ሰላም ይመስላል።
እና መረራ ሆይ! ፈራሁ!! በጣም ፈራሁ።
እድል ካገኘህ ወጣቶች ወደ በቀል እንዳይሄዱ ምከር። ይህን የሚፈጽሙት ያበዱ ግለሰቦች እንጂ የህዝብ ወኪሎች አለመሆናቸውን ተናገር እባክህ። የሚመጣው ዘመን በጣም ያስፈራል። የተቆጡ ወጣቶች ጊዜው ሲደርስ ሊፈጽሙ የሚችሉት የበቀል እርምጃ አሳስቦኛል።
ወዳጄ መረራ! በዚህ ክፉ ጊዜ በተቻለህ መጠን እንደቀድሞህ ቀለል አደርገህ ወጣቶችን አርጋጋ። ልክ እንደ ቀድሞህ ቀልድ እየጨመርክ አውጋን። በተቀረ አኩሪ ታሪክ ሆነሃል። እንኩዋን ደስ ያለህ!!

2 comments:

Tech with Estif said...

THANK YOU !!! "THE BLACK SOIL OF ADHA"

Anonymous said...

What is the solution for Ethiopian to leave peacefully Ever after considering the current situation? I will like to know your solution since I belive your wisdom will help a lot for present and future generation of ethiopian and eastafrica brothers and sisters to create #Great_Oromo #Great_Amhara #Great_Somali #Great_Tigray #Great_Afar #Greatest_other_other_People_Of_Ethiopia