ባለፈው ሃሙስ ቃለመጠይቅ ለመስጠት ወደ
VOA ቢሮ ሄጄ ነበር። አብዛኞቹን ጋዜጠኛች አገኘሁዋቸው። ቀደም ብዬ በአሳቤ የምስለውን ምስል አላገኘሁም። የአማርኛ፣ የትግርኛ፣
የኦሮምኛ ቋንቋ ጋዜጠኞች በአንድ አዳራሽ ውስጥ (Cubicals) በአንድ ላይ ነበሩ። በየቋንቋው በተለያየ ቦታ የሚገኙ መስሎኝ ነበር።
ቆንጂት ታየ፣
ሰለሞን ክፍሌ፣ ትዝታ በላቸው፣ ነሞ ዳንዲ፣ ጃለኔ፣ አሉላ ከበደ፣ ሄኖክ ሰማዝግሄር፣ ምንያ አፍወርቂ፣ በትረ፣ ተወልደ ወልደገብርኤል፣
አዳነች ፍስሃዬ፣ ጽዮን ግርማ፣ ሰለሞን አባተ፣ ሳሌም ሰለሞን፣ ደሳለኝ እና ሌሎችንም ጋዜጠኞች አገኘሁዋቸው። አዲሱ አበበ አልነበረም።
የታለ ብዬ ስጠይቅ “እረፍት ላይ ነው” ብለው ነገሩኝ።
ከተወልደ ጋር በትግርኛ፣ ከትግስት ገሜ ጋር በግማሽ ኦሮምኛ፤ በግማሽ አማርኛ
ቃለመጠየቅ ሰጠሁ። ትግስት “ስምህን ለአድማጮቼ ብትነግራቸው?” ብላ ስትጠይቀኝ፣ “መቃን ኬኛ ጋዳ ጋብራብ” ብዬ ተናገርኩ። ከአማርኛ
ፕሮግራም ጋር ለሰፊ ቃለመጠይቅ ቀጠሮ ተቀብያለሁ። አብዛኞቹ “የኑረነቢ ማህደር”ን ገዝተው ወሰዱ። ስራዬን ከጨረስኩ በሁዋላ ከትግስት
ገሜ ቢሮ መቀመጫ ላይ ቁጭ አልኩና ጥቂት አወራን።
No comments:
Post a Comment