እነሆ! በዛሬው እለት ወደ ኦሮሚያ ጢኖ
በመጓዝ ላይ ነኝ። ኦሮሚያ ጢኖ
ማለት ሚኒሶታ ናት። ሚኒሶታ ከ33 ወራት
በፊት ሄጄ ነበር። የበረዶው ወራት ካለፈ በሁዋላ የሚኒሶታ ሁዳድ አድአ በርጋን ይመስላል። ቅጠሎች ሲለመልሙ እንደ
ኦቦ ጩቃላ ተራራ ጫካ ጠል ያዝላሉ። ወደ ሚኒሶታ የማደርገው ጉዞ መንፈሴን ይኮረኩረዋል። ሚኒሶታ በጣም ብዙ
ጓደኞችን አገኛለሁ። ዋቃ ጉራቻ ፈቃዱ ከሆነ የሚቀጥለውን መጽሃፍ የማስመርቀው ቢሾፍቱ ይሆናል። ይታየኛል። በምጽሃፍ ምረቃው ላይ ከበከጆ፣ ከገላን፣ ከቱሉዲምቱ፣ ከቱሉፈራ፣ ከደንካካ፣ ከበደገባቤ፣ ከድሬ፣ ከሎሜ፣ ከሉጎ፣ ከአዳማ፣ ከጋራቦሩ፣ ከጨፌዶንሳ ጭምር ይመጣሉ። አማርኛ ማንበብ ቢቸግራቸውም እንኳ እንዲሁ ከኔ ጋር ለመጨዋወት ሲሉ ይመጣሉ።
1 comment:
I WISH TOO..."THE BLACK SOIL OF ADHA"
Post a Comment