ለማ መገርሳ
ለማ መገርሳ በዳዴኡኦ (OPDO) በኩል ከወያኔ ጋር ግንኙነት ባደረገባቸው የመጀመሪያዎቹ
አመታት ለጥቂት ወራት ሰላሌ ተወስዶ ታስሮ እንደነበር መረጃዎች አሉ። የታሰረበት ምክንያት ወያኔ ከሚፈልገው በላይ የኦሮሞ ብሄርተኛነት
ዝንባሌ አንጸባርቆ እንደነበር ሰምቻለሁ። በመቀጠል ለማ መገርሳ ሰላሌ እስር ቤት ሳለ የወቅቱ የአገሪቱ የጸጥታ መስሪያ ቤት ሹም
የክንፈ ገብረመድህን እጆች ነካኩት። ለማ ከእስር ከተፈታ በሁዋላ
እንደ ቡርቃ ወንዝ ድምጹ ሳይሰማ በስራ ላይ ቆየ። የቡርቃ ወንዝ ዝምታ አብቅቶ ኦሮሚያ በኦሮሚያውያን ቁጣ ስትናወጥ ለማ መገርሳም
አብሮ ብቅ አለ። ለማ መገርሳ “በኦሮሞ ህዝብ አብዮት የተወለደ የኦሮሞ ህዝብ ልጅ?” ወይስ “ድብቅ አጀንዳ ይዞ የመጣ አክተር?”
በዚህ ጉዳይ ላይ የግል አስተያየቴን በቅርቡ አስነብባለሁ።
No comments:
Post a Comment