Wednesday, February 10, 2016

የመሳይ ከበደ በር

         ዛሬ ላይ ቆመው ነገን ለማወቅ የሚችሉ ሰዎች “ነቢይ” ሲባሉ ኖረዋል። በዘመናችን ቋንቋ “የፖለቲካ ተንታኝ” ማለት ይሆን? ይህን የሚገልፅ አንድ አባባል አውቃለሁ፣ “ትናንት ታሪክ ሆኖአል፤ ዛሬ ስጦታ ነው፤ ነገ ደግሞ ምስጢር”
 
መሳይ ከበደ በመጨረሻ የፃፈውን መጣጥፍ ሳነብ (Then and Now: A Rejoinder to my Critics)  ‘ይህ ፕሮፌሰር ኢትዮጵያን ከመፍረስ ሊያድኑ ከሚችሉ ሂቃን አንዱ ሊሆን ይችላል’ ብዬ ተስፋ አደረግሁ።
ምክንያቱም መሳይ አይነኬ የተባሉ አመለካከቶችን በድፍረት መተቸት መቻሉን አይቻለሁ። ማለትም “ለአንድነት ሃይሎች” ወደ አንድነት የሚያደርስ የመግቢያ አዲስ በር መክፈት ችሎአል። መቸም ወያኔ ጉዞውን እንደጨረሰ ስምምነት ያለ ይመስላል። ያልታወቀው ወዴት አግጣጫ እንደሚገነደስ ነው። ምእራባውያን ወይም አሜሪካ የወያኔን ስርአት ለማቆየት እየጣሩ መሆኑ ይታሰባል። ስርአቱ በከዘራም ሆነ በአንካሴ ተደጋግፎ መቆም ካስቸገራቸው ግን አይኖቻቸውን በመሃረም እያባበሱም ቢሆን መቃብሩን ይቆፍሩለታል።

በአካባቢያችንም ሆነ በሌሎች ተንታኞች የሚፃፉ አስተያየቶችን ስናነብ ኢትዮጵያ መንታ መንገድ ላይ መቆሟን እንገነዘባለን። ይህም ከማይቀረው አንድ መተራመስ በሁዋላ ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊት አገር ሆና በአስተማማኝ መሰረት ላይ ቆማ ትቀጥላለች፤ አሊያም መረራ ጉዲና አራተኛው ይሆናል (Scenario) ብሎ እንዳስቀመጠው ኢትዮጵያ በስብሳና ተንጣ እንደ ሃገር ትፈርሳለች። (መፍረስ ቢከሰት በፍርስራሹ ላይ ሌላ የአዲስ ታሪክ መሰረት እንደሚጀመር በአእምሮአችን መያዝ ይገባል።) እና መንታ መንገዶቹ እነዚሁ ናቸው። ስለ ኢትዮጵያ መፍረስ ጉዳይ መናገር ክፉ በመመኘት አይደለም። አፍጥጦ እየመጣ ያለውን እውነት ከወዲሁ ማወቅ መፍትሄ ለመፈለግ ያግዛል በሚል ነው። ከመነሻው መሳይ ከበደ ኢትዮጵያን ከመፍረስ ሊያድኑ ከሚችሉ ሂቃን አንዱ ሊሆን ይችላል ብዬ ተስፋ ያደረግሁባቸውን በር ከፋች አመለካከቶች ከብዙዎቹ ጥቂቶቹን በዚህ መጣጥፍ እያነሳሁ የግል አስተያየቴን አኖራለሁ።
 
 መሳይ እንዲህ ይላችሁዋል፣

  “The most important complaint of the Oromo is that the Ethiopian discourse has always marginalized their contribution and identity in favor of a unilateral assimilation that favored Amhara and Tigreans.”

እውነት ነው። በዘመነ ደርግ፣ “የኢትዮጵያ ብሄረሰቦች ጌጦቻችን ናቸው” ይባል ነበር። አባባሉ ሲመረመር ያስቃል። በጣም ያስቃል። እንግዲህ አንዲት ሴት አለች እንበል። ያቺ ሴት አማራ ናት። ጠጉሯ ላይ፣ እጇ ላይ፣ ጆሮዋ ላይ፣ አንገቷ ላይ፣ እግሯ ላይ በተለያዩ ጌጦች ተውባለች። እነኛ ጌጦች ብሄረሰቦች ናቸው። የኢትዮጵያ ብሄረሰቦች ህልውና የአማራና (በከፊል ደግሞ የትግሬን) ባህል ማድመቅ ሆኖ ኖሯል። ይህ ሁኔታ የአሰቃቂ ውጊያዎች መነሻ፤ የመራራ ቅሬታዎች፣ የረጅም ማኩረፎች፣ የአደገኛ ዝምታዎች ምክንያት ሆኖ ኖሮአል። በቀጥታ ለመግለፅ በዚህ አመለካከት ወይም የአገዛዝ ስርአት የአማራ ህዝብ ተጠቃሚ አልነበረም። ተጠቃሚ ስላልነበረም ነው፣ በግልፅ መነጋገር እና እውነቱን ማመን አስጊ ወይም በታታኝ ሊሆን የማይችለው። ምናወጋው ስለ ገዢ መደቡ ነው። በገዢ መደቡ ውስጥ በግለሰብ ደረጃ አማራ ያልሆኑም ነበሩበት። ሎሬንሶ ታእዛዝ እና ጃጋማ ኬሎ አብነት ናቸው።

የመሳይ ጥቅሶች ይቀጥላሉ፣

“The demand that Oromo protesters turn their issues into a national or Ethiopian cause seems to repeat the past practice. Following the inescapable reality of the political fragmentation of the country, the Oromo rose up for their own cause, sacrificed their life, and now they are told that they should transfer their heroic deeds to the larger Ethiopian entity even though that entity remained aloof! I want to remind that most of the young Oromo protesters have no idea of Ethiopia as a unitary nation: as the established political system forces them to do, they see Ethiopia as a collection of different nations. Just as Kenyans are not expected to fight for Ethiopians, so too it is not surprising if the Oromo present their demands in terms of Oromo concerns.”

 ይህም እውነት ነው፤  በ2014 ኢትዮጵያ እና ናይጄሪያ ለአፍሪቃ ዋንጫ ማጣሪያ እግርኳስ ሲጫወቱ በርካታ የኦሮሚያ ወጣቶች የናይጄሪያ ደጋፊ ነበ። በወቅቱ ይህን እውነት በመፃፌ የደረሰብኝ ውግዘት ዝሆን የሚሸከመው አልነበረም። እውነትነቱን ዛሬ መሳይ ከበደ አረጋገጠው። ፕሮፌሰር መሳይ ከበደ በከፈተው በር ብዙዎች ከአክራሪ አስተሳሰባቸው ተላቀው ወደ እውነቱ ይመጣሉ ተብሎ ይጠበቃል። ለነገሩ ጉዳዩ ፕሮፌሰር መሳይ ከገለፁት በላይም ነው። ዋሽንግተን ዲሲ ወይም ሚኒሶታ ሄደህ አንዱን ኦሮሞሃበሻ ነህ?ወይምኢትዮጵያዊ ነህ?ብለህ ብትጠይቀው እንደሰደብከው ሊቆጥር ይችላል። አንድ ኦሮሞ ቆሞ ሳለ በድንገት ከሁዋላው ሄደህ የኢትዮጵያን ባንዴራ ብታለብሰው፤ እባብ አንገቱ ላይ ያሰርክበት ያህል ሊቀፈው ይችላል። ይህ እውነት ነው። ከዘመናችን ወጣት ብሄርተኛ ኦሮሞዎች ጋር ሲነፃፃሩ እነ ሌንጮ ለታ፣ እነ መረራ ጉዲና፣ እነ በቀለ ገርባ፣ እነ ኢብሳ ጉተማ መንዜ ማለት ናቸው። ያለምንም ማጋነን ባሮ ቱምሳ በቁመቱ መርዘም ብቻ ሳይሆን በአመለካከቱም ጭምር ቤካን ጉልማን ተክቶታል። በተለምዶ OLF አክራሪ ነው ይባላል። OLF ግን የህዝብ ውሳኔን እንደሚቀበል ይናገራል።አክራሪ የአንድነት ሃይሎች OLF በላይ ፈተና የሚሆንባቸው የዘመናችን የኦሮሞ ወጣት ነው። ምክንያቱም በጥቅሉ ለመገምገም እንደሚቻለው እንኳን መረራ ጉዲናን OLF እንኳ ተላስልሶአል የሚል ወጣት ውልድ ተፈጥሮአል።
የመሳይ ከበደ እውነት አዘል ጥቅሶች እንዲህ ይቀጥላሉ፣
“The request to append the label ‘Ethiopia’ to the protests is an invitation to commit historical robbery; more importantly, it forgets that Oromo courageous fight against the TPLF machine is how they rehabilitate themselves and become makers of their own history and, through them, of the history of Ethiopia. Clearly, such a request lacks fairness, to say the least. Who would blame the Amhara if they turn their protest against the ceding of tracts of land in Gondar to Sudan into an Amhara issue?”
የአማራ ጉዳይ ለአካባቢያችን እንቆቅልሽ ሆኖብናል። “አማራ አለ ወይስ የለም?” የሚለው ጥያቄ ማከራከር ከጀመረ ይኸው 26 አመታት ሞላው። ጥያቄውን በቅድሚያ ያነሳው መንግስቱ ሃይለማርያም ነበር። “አማራ የሚባል ብሄር የለም” ብሎ ነገረን። መስፍን ወልደማርያም ከደርግ ውድቀት በሁዋላ የመንግስቱን አባባል ደገሙት። “ጎንደሬ፣ ጎጃሜ፣ ሸዌ፣ ወሎዬ እንጂ አማራ የሚባል ጎሳ ወይም ዘር የለም” አሉ። ዶክተር አስራት ወልደየስ ደግሞ ተነሱና “አማራ የሚባል ዘር አለ። እኔም አማራ ነኝ” አሉ። ይህንኑ ለማረጋገጥም “መላው አማራ” የሚል ድርጅት መሰረቱ። አስራት ሲሞቱ ሃይሉ ሻውል ድርጅቱን ወረሱትና፣ “አማራ የሚባል ዘር የለም። ወደድሽም ጠላሽም ሁልሽም ኢትዮጵያዊ ብቻ ነሽ። ስለዚህ ‘መላው አማራ’ የሚለውን ‘መላው ኢትዮጵያ’ ብለነዋል” አሉ። በዚህ መካከል ብዙ ዜጋ ተንገላታ። አመታትም ነጎዱ። የሃይሉ ሻውል ተከታዮች እንግዲህ ኢትዮጵያ ሲሉ፣ ኦርቶዶክስ ሃይማኖት፣ አማርኛ ቋንቋ፣ አረንጓዴ-ቢጫ-ቀይ ባንዴራ፣ ሹሩባና ጥበብ ልብስ ማለታቸው ነው። ከዚያ ባሻገር ያለው ባህልና ቋንቋ በውስጠ ታዋቂነት አጃቢና አዳማቂ ሆኖ እንዲቆይ ይሻሉ። እንዲያም ሆኖ የኢትዮጵያዊነትና የአማራዊነት መስመር መለያው ዛሬም ድረስ ግልፅ አይደለም። ከጥቂት አመታት በፊት ደግሞ፣ “ሃይሉ ሻውል አማራ የለም ብለው አማራውን አስጠቁት። ስለዚህ ‘ሞረሽ’ የሚባል የአማራ ጠባቂ ድርጅት መስርተናል” የሚሉ ወገኖች ተነሱ። እነርሱም ተቃዋሚ ፈላባቸው። ፕሮፌሰር ጌታቸው ሃይሌና ሰአሊ አምሳሉ ገብረኪዳንም እንዲሁ በዚሁ ሰሞን በአማራ መኖር አለመኖር ጉዳይ በመሟገት ላይ ናቸው። አሁንም አልለየለትም።
ረጅም ዘመን የፈጀው ይህ ሙግት ለወያኔ ምቹ የመጋለቢያ ክፍት ሜዳ ስለተወለት ሁለቱንም ወገኖች እያበረታታ አማራን በቆረጣ እና በደፈጣ ያመናምነው ያዘ። አልፎ ተርፎ ወልቃይት የሰፈሩት መጤ የወያኔ ደጋፊዎች “አማራ ከክልላችን ይውጣ” የሚል ሰልፍ እስከማካሄድ ደረሱ። ድርቅናቸው ያስገረመው ወልቃይቴ፣ አፉን በጋቢ ሸፍኖ፣ “ማርያም ምኑን አሰማሺኝ!? ቅዱስ ጂወርጊስ ታደገን!” እያለ የመጤዎቹን ሰልፍ ዳር ቆሞ ሲታዘብ ዋለ። “አማራ ከኦሮሞ ቀጥሎ ትልቁ ብሄር” ሲባል እንዳልኖረ አሁን ደግሞ፣ “አማራ እንደ ዋልያ ሊጠፋ ነው” እስከሚል ተገላቢጦሽ ለመስማት ደረስን። ከሳንቃ በር ገደል ላይ እየተፈጠፈጠ በመሞት ላይ ያለውን ዋልያ ከአማራ ጋር ማመሳሰል ስላቅ ቢሆንም ጥቂት እውነት አያጣውም። በዚህ ዘመን ‘አማራ የሚገኘው አዲሳባ እና ዋሽንግተን ዲሲ ላይ ብቻ ነው’ ብለው የሚሞግቱም አሉ። እና መሳይ ከበደ እውነቱን ነው። The game is ነግ በኔ::

ፕሮፌሰሩ በመቀጠል እንዲህ ይላችሁዋል፣

 “…The fight for a unitary nation should have been waged while the TPLF was battling the Derg. It is now too late and there is no going back. Going back would mean war and, if the Ethiopian state survives, the cost would be the institution of another dictatorial system. How else, if not by blood and fire, would you impose unity after two decades of unrestricted ethnicization? … You do not present conditions when people rise and fight an oppressor that also happens to be your own oppressor. You join the fight and only then can you make the issue of unity a common cause. Those who simply watch cannot present conditions to people being beaten, killed, and imprisoned. To make your support conditional is to forget that you are also chained, beaten, killed, and imprisoned by the same oppressor. I find it strange, I repeat, that the sharing of the same fate with the Oromo does not trigger the sense of solidarity…”

ልብ ያለህ ይህን ስማ። ኦሮሞ ለመብቱ እየታገለ፣ እየሞተ ሳለ አንተ ዳር ላይ ቆመህ “የኢትዮጵያን ባንዴራ ካልለበስክ፣ ሃበሻ ነኝ ካላልክ፣ ለተክልዬ ካልሰገድክ በአመፁ አላግዝህም” ማለት ምን ማለት ነው? ትናንት ያነሳሁትን ልድገመው። የኦሮሞ ህዝብ ብቻውን ታግሎ አፋኙን ስርአት ካስወገደ ቀጥሎ ምን ይሆናል? ምላሹን እዚህ አልፅፍም። ግልፅ ነው። ለነገሩ የመተጋገዙ ጥሪ የተደረገው ለአብሮ መኖር ይጠቅም ዘንድ እንጂ፤ ሌሎች ካልተሳተፉበት ወያኔን ማስወገድ አይቻልም ከሚል አይደደለም። የሞረሽ መሪዎች ከኦሮሞ ህዝብ አመፅ ጋር ተባብረው ለምን ወያኔን እንደማይታገሉ ሲጠየቁ፣ “ትእግስት ፍርሃት አይደለም” ይላሉ። ፍርሃት ግን በትእግስት ካፖርት ስር ሊሸሸግ ይችላል። አምላክ ነፍሱን በገነት ያኑራትና መለስ ዜናዊን አልወደውም ነበር። የማልወደው ቡፋ ስለነበር ነው። ቡፋነቱ እንዳለ ሆኖ አንዲት የምወድለት አሪፍ ጥቅስ ግን ነበረችው። “መታገስ እና መልፈስፈስ ለየቅል ናቸው” ይል ነበር። የተልፈሰፈሰ ሰበብ ባይፈጥር ይሻለዋል። ቢያንስ ግን ዝም ይበል። ዝምታም ቋንቋ ነው።

የመሳይ ከበደ ጥቅሶች ቀጥለዋል…

“…Nor do I understand how those who rightly claim to be the creators of modern Ethiopia, namely, Amhara elites––of course, in partnership with the Oromo, as evinced by the prominent role of Ras Gobena and other Oromo leaders, to remind those who would be tempted to forget it––do not come to the forefront of the fight for Ethiopia instead of making their intervention conditional on the acceptance of their demands. To pose conditions eliminates the unconditional commitment to Ethiopia, which is precisely what they accuse the Oromo of lacking. If you want an unconditional commitment to Ethiopia, then begin by showing your own unrestricted dedication by joining the Oromo despite the missing Ethiopianism, for only thus you can win them over.”

ሌላው ሁሉ ተቀባይነት ያለው ሆኖ፣ አንድ ነጥብ ላይ ግን ለማስታወስ ያህል … ጎበና ዳጪ ተከድቶ እና አዝኖ ነበር የሞተው። በርግጥ ራስ ጎበና ኢትዮጵያ የተባለች አገር ለመመስረት በተደረገው ጦርነት የገዛ ወገኖቹ ላይ ጉዳት አድርሶአል። ሁዋላ ግን ተፀፅቶአል። ፀፀቱንም ለልጅ ልጆቹ አውርሶአል። የልጅ ልጆቹም በአያታቸው ድርጊት ተፀፅተው የአያታቸውን ስህተት ለማረም ሞክረዋል። ተድላ ባይሩ በሰራው ስራ ተፀፅቶ ወደ ትግል ሜዳ እንደወጣው ሁሉ፤ የጎበና ዳጪ የልጅ ልጅ ዳንኤል አበበ የኦሮሞን ህዝብ መብት ለማስከበር ብዙ ሰርቶአል። በተለይ የጨቋኞች መናኸሪያና የበዝባዦች ግብር መሰብሰቢያ ማእከል የሆነችውን አሰላ ከተማን ወደጎን በመተው ዝዋይ ዱግዳ ላይ የአርሲን ዋና ከተማ ለማነፅ በመሞከሩ (ማለትም የዛሬዋን ባሌ ሮቤ የመሰለች የኦሮሞዎች ከተማ ለመስራት በመነሳቱ) ዋጋ ከፍሎበታል። ከዚያም አልፎ ዳንኤል የመጫ እና ቱለማ ማህበርን መርዳት በመጀመሩ አጤ ሃይለስላሴ አውሮፕላን ላይ በተጠመደ ፈንጂ ገድለውታል። ሬሳው እንኳ አልተገኘም። ዳንኤል አበበ ህይወቱን ሲከፍል ጥቅም ቀረብኝ ብሎ አልነበረም። በዚያን ዘመን ዳንኤል የግል አውሮፕላን የነበረው ከበርቴ ነበር።  ጎበና ዳጪ የሰራውን ስህተት የልጅ ልጁ ለማረም መሞከሩ ለተጨቆነ ህዝብ መብት መከበር የተከፈለ ዋጋ ነበር። ጎበና ስሙ ስለተነሳ ቆነፀልኩት እንጂ የመሳይ ከበደን አሳብ እየተቃወምኩ አይደለም።

እነሆ! የመሳይ ከበደ የመጨረሻ ጥቅስ፣

“…To present condition is also to endorse the divided-and-rule police of the TPLF. Indeed, in being bystanders in this trying and crucial moment for the Oromo, what message are we sending to them? Are we not telling them that their cause and their atrocious mistreatment are not of our concern? How would they feel Ethiopian when those who claim to be Ethiopian turn their back on them? This is to say that the Oromo uprising gives us the unique opportunity both to defeat the TPLF and forge a new unity by our struggle against the common oppressor. Let us remake Ethiopia, this time through the concrete solidarity and unity of the oppressed!”

መሳይ በጥቂት ቃላት በትክክል አስቀምጦታል። ወንድምህን ወንድሜ ነው ብለህ ካመንክ በሞትና በህይወት ትግል ላይ ባለበት ወቅት እንዴት ወንድምነቱን እንዲያረጋግጥልህ ቅድመ ሁኔታ ታቀርባለህ? ከቅድመ ሁኔታ ጥያቄህ መረዳት የሚቻለው ከመነሻውም ወንድሜ ነው ብለህ እንደማታምን ነው። ማለትም ጌጥህ ብቻ ነበር ማለት ነው። ተሸፋፍኖ የኖረውን ይህን የተዛባ ሁኔታ ግልፅ በማድረጉ፤ ፕሮፌሰር መሳይ Galatoomaa ሊባል ይገባዋል። ማለትም በኦሮሞ ህዝብ ስም እናመሰግናለን።

ከጥቂት በላይ ኦሮሞ ልሂቃን የመሳይን ፅሁፍ በአክብሮት ሲቀባበሉት አይቻለሁ። መሳይ በዚህች በፃፋት ሁለት ገፅ እውነት ምንጊዜም የኦሮሞ ህዝብ ባለውለታ ሆኖ ይቆያል። ምላሹን ከአሁኑ እያየነው ነው። ኦሮሞዎች በጎ ቃላትን ወደ መሳይ እየላኩ ነው። ሌላው ቀርቶ OLF አባላት እንኳበርግጥ ይህን የፃፈው መሳይ ነው?” ብለው ሲነጋገሩ ሰምቻለሁ። መሳይ በዘሩ አማራ ይመስለኛል። የኦሮሞ ልሂቃንን ቀልብ መሳብ የቻለ የመጀመሪያው አማራ መሆኑ ነው። ከዚህ ቀደም በኦሮሞ ህዝብ ጥያቄ ላይ እንዲህ በግልፅነት የፃፈ አንድም አማራ አላውቅም። መሳይ በፅሁፉ የኦሮሞ ልሂቃንን ቀልብ   ለመሳብ ልዩ ጥበብ አልተጠቀመም። መቶ ገፅ መፃፍም አላስፈለገውም። ጥቂት እውነት ተነፈሰ። የተጨቆኑትን ወገኖች እውነት ከልቡ ማየት ቻለ። እውነትን ለመሸፋፈን አልሞከረም።በሁሉም አቅጣጫ የሚመጡ አክራሪዎች ኢትዮጵያን ያፈርሷታል።ብሎ ከልቡ ማመኑን በቃሉ አረጋገጠ። በጥቅሉ መሳይ ከከበበው የምቾት ግቢ ብቅ ብሎ ሌላ ለብዙሃን የሚበጅ የአንድነት የአማራጭ መንገድ ማየት በመቻሉ ይመስለኛል። እናም ጥቂት እውነት በመናገር ብቻ በአንድነት እና በመከባበር አብሮ ለመኖር የሚያስችል በር መክፈት እንደሚቻል ታየ። ርግጥ ነው፤ ፕሮፌሰር መሳይ ይህን በማድረጉ ዋጋ ይከፍል ይሆናል ብዬ እገምታለሁ። ዝነኞቹ እነ ስድብኤል እንዲሁ እንደዋዛ  ይተውታል አይባልም። እና ለወቀሳውም ሆነ ለሙገሳው ቆዳውን አጠንክሮ መቆየት ይገባዋል።

ኪሩቤል በቀለ ሰሞኑን በለቀቀው በራሪ ኢሜይል አንዲት አሪፍ አባባል አስፍሮ ነበር። “…እዚህ ዛሬ የምንንጫጫ ግለሰቦች ሁሉ ከመቶ አመታት በሁዋላ አንዳችንም አንኖርም።” ኪሩቤል እውነት ብሏል። ከመቶ አመታት በሁዋላ መፃፅፋችን ቀርቶ፤ መፅሃፋችን እንኳ ለመታወሱ እርግጠኛ አይደለንም። ወንድሜ ሆይ! ረጅም ፎቅ ወይም ቄንጠኛ ቪላ ገንብተህ ሊሆን ይችላል። የገነባኸው ማስታወሻህ እንደሚሆን ግን ርግጠኛ አይደለህም። የልጅ ልጆችህ በሃብት ክፍፍል ይጋጩና በርካሽ ዋጋ ጆሮውን ይሉት ይሆናል። ከዚያ በሁዋላ ለስምህ ብለህ የደከምክበት የላብህ ቅርስ የማታውቀው የሌላ ሰው ንብረት ይሆናል። ወንድሜ ሆይ! ልጆች ወልደህ ሊሆን ይችላል። እሱም ቢሆን ማስታወሻህ ሆኖ አይቆይም። የልጅ ልጅህ ስለአባቱ እንጂ ስለ ቅድመ አያቱ ብዙም ግድ አይሰጠውም። የዚህ አባባሌ ቁምነገሩ ምንድነው? ትናንት ወይም ነገ የኛ አይደለም። ዛሬ ግን ስጦታ ነው። ዛሬን ለበጎ ከሰራንበት፤ እውነትን ለመግለፅ ከተጠቀምንበት ድርጊታችን ቢጎዳን እንኳ ወደ ታሪክ እስክንቀየር ቢያንስ መንፈሳዊ እርካታ አናጣበትም። ፕሮፌሰር መሳይ ሆይ! በድጋሚ GalatoomiGalatoomaa.


Gadaa Ghebreab   የቅዳሜ ማስታወሻ    www.tgindex.blogspot.com    ttgebreab@gmail.com     feb 10 2016  

11 comments:

Tech with Estif said...
This comment has been removed by the author.
Anonymous said...

በመጀመሪያ ደረጃ አማራ ሚባለዉ ብሄር ከማንም በላይ በሳል አእምሮ ባለቤት የሆነ ህዝብ ነዉ፡፡ ባለፉት አርባና ሃምሳ አመታት የተደረገዉን በሙሉ ተመልክቷል፤ ገፈት ቀማሽም ሆኗል፡፡ ስለሆነም በአማራ ስም በመነገድ ብዙዎቹ አትርፈዉበታል፡፡ አማራ ነን በሚሉ የስልጣን ጥመኞች ሲጨቆን ኖሯል፤ ከዚህ በኋላ የማንም ፖለቲካ ማስፈጸሚያ አይሆንም፡፡ ካስፈለገ ኢትዮጵያ ትኖራለች፤ የማይሆን ከሆነም መበተን ትችላላችሁ፡፡ ኢትዮጵያዊነት የአማራ ጉዳይ ብቻ አይደለም፤ አማራም ሃገርና ክልል ጀግና ህዝብ አለዉ!!
ስለዚህ እባካችሁ አማራን ተዉት!!! ከፈለጋችሁ መገንጠል መብታችሁ ነዉ!! አማራ አልከለከላችሁም!! ‹‹ አህያዉን ፈርቶ ዳዉላዉን›› ነዉ ያለ የሃገሬ ሰዉ!!! ኦሮሞ የተጣላዉ ከህዉሃት ጋር ከሆነ፤ ኦሮሞ የተጣላዉ ከኦህዴድ ጋር ከሆነ አማራ ምን አገባዉ!! እንደጀመራችሁ እናንተዉ ጨርሱት! አማራ ከዚህ በኋላ ለራሱ መብት ብቻ ይቆማል!! ስጋት አይግባችሁ! በቅርቡ በሁለት አመታት ዉስጥ ማን እንደሆነ ታያላችሁ! እድሜ ብቻ ይስጠን፤ አማራ ከሃገራችን ይዉጣ ትላላችሁ! ኦሮሚያ የኦሮሞ ናት ትላላችሁ! ታዲያ አማራን እዝህ ዉስጥ ምን ጥልቅ አደረገዉ! ሁለታችሁ ስትጣሉም አማራን ማጥላላት ስትፋቀሩም አማራን ማጥላላት! አረ ጎበዝ ይደብራል! ከፈለጋችሁ ሁለታችሁም መገንጠል ትችላላችሁ!! በአሁኑ ወቅት እኮ አማራ የሚባል ብሄር በክልሎች በከተሞች ካልሆነ በቀር በገጠሩ ክፍል የለም!! ስለሆነም እንዳትሸወዱ ጎበዝ! ኢትዮጵያዊነት፣ አንድነት የአማራ ጉዳይ ብቻ አይደለም!! አብዛኛዉ የተማረዉ የትግራይ ህዝብ በሁሉም ክልሎች ላይ ተበታትኖ ይገኛል! አብዛኛዉ ነጋዴ የጉራጌ ህዝብ በሁሉም ከተሞች ተበታትኖ ይኖራል! ብዙ የኦሮሞ ህዝብ በአማራ እና በቢኒሻንጉል ክልል ይኖራል! ታዲያ ኢትዮጵያ ለምን በአንድ ጀምበር ብትንትን አትልም! አማራ ከሌለ፤ ኢትዮጵያዊነት የለም!!
ስለሆነም እደግመዋለሁ እባካችሁ አማራዉን ተዉት!!! ተስማምታችሁ የፈጠራችሁትን የጎሳ ፖለቲካ በማራመድ ‹‹ተስማምታችሁ ዝረፉት››!! ‹‹የጎሳ ፖለቲካ የማር ቀፎ ነዉ›› እንዳለዉ ጸሃፊዉ የለመዳችሁትን ማር በብሄር ሰበብ እየቆረጣችሁ ብሉ!! አማራን ተዉት አቦ!! ሁለታችሁም የ16ኛዉ ክፍለ ዘመን አስተሳሰብ የያዛችሁ ‹‹ታጥቦ ጭቃ›› ናችሁ!!

Anonymous said...

"....መሳይ በዘሩ አማራ ይመስለኛል...."
አንተ ዘረኛ፣በመሰለኝ እና በደሳለኝ የምትፅፍ የሻቢያ ቡችላ!

Unknown said...

Thank you indeed Gadaa for your usual deep insights.
Those who talks about the balcanised Ethiopia which were created on oromos blood at this crucial time are in never ending nightmare.
Whether they stand with oromo or not the oromos will fight to the end until the last man fall.
We will liberate not only oromo and oromia but also Amhara and Ethiopia.
One thing ethiopians in every corner of the world have to understand is that,the so called diaspora polatics established underAmhara name are not the representative of amhara it is rather the club of oppressors who migrated to protest the "land to the tillers" proclamation.
On top of the they have no public base, no one is ready to be mobilized by their old rhetoric which brought ethiopia to destruction edge.
They are an old wine in a new bottle.
I would like to say thank you to you for not bitting the hands that fed you like those illusionned so called ethiopianists.
Ye qajimaw gorgis edimena tena yistih.

Unknown said...

Thank you indeed Gadaa for your usual deep insights.
Those who talks about the balcanised Ethiopia which were created on oromos blood at this crucial time are in never ending nightmare.
Whether they stand with oromo or not the oromos will fight to the end until the last man fall.
We will liberate not only oromo and oromia but also Amhara and Ethiopia.
One thing ethiopians in every corner of the world have to understand is that,the so called diaspora polatics established underAmhara name are not the representative of amhara it is rather the club of oppressors who migrated to protest the "land to the tillers" proclamation.
On top of the they have no public base, no one is ready to be mobilized by their old rhetoric which brought ethiopia to destruction edge.
They are an old wine in a new bottle.
I would like to say thank you to you for not bitting the hands that fed you like those illusionned so called ethiopianists.
Ye qajimaw gorgis edimena tena yistih.

Unknown said...

Thank you

Unknown said...

Another wonderful piece. By the way that Ethiopia vs Nigeria game had similar experience in AA stadium too. Many of us were for Nigerians. 'Ethiopians' wanted to fight after the game.

Anonymous said...

chingaf...just like 'your country'

Unknown said...

Tesfaye’s analysis of Dr Mesay’s commentary helps those who rather want bury their heads in the sand. Mesay looks at the past, considers the present and envisions the future. An opinion leader that our time needs.

Anonymous said...

Your words are sharper than a blade.I love your style of expression.

Tadele Kenea said...

?? ???? ?????? ??? ??? ??????? ??? ?? ?????? ???? ??? ????? ??? ?? ????? ??? ????? ???? ??? ????? ???? ??? ??? ???? ????? ??????'??? ????? ??? (????? ????? ???? ???? ?? ???? ???? ?????)? ???? ??? ?? ????? ???? ?????? ??? ????? ???? ???? ?????? ?? ????? ????? ??? ???'??? ?? ????? ???? ?????? ???? ???? ?? ??? ??? ?????? ??? ????? ?? ?? ?????? ??? ??? ???? ????? ??? ?? ?????? ?????????? ?????? ??? ???? ???????? ????????? ??? ?????? ??????? ????? ??? ???? ?? ????? ???? ???? ??? ?? ???? ??????? ?? ???? ??? ??? ?????? ????? ???? ??????? ????? ??? ?? ???? ??????? ???? ????? ?????? ????? ?? ????? ??????? ?? ???? ????? ??????? ????? ????? ???? ?? ??????? ???? ????????