Thursday, December 18, 2014

ታሪክ የአሸናፊዎች ነው



ከተስፋዬ ገብረአብ (Gadaa)
         
“ሁሉም ነገር ወደ ጦር ግንባር” በሚል ርእስ የተፃፈውን የጄኔራል ውበቱ ፀጋዬን መፅሃፍ እያነበብኩ ነው። ከኤርትራ ነፃነት ወዲህ ኢትዮጵያውያን ኤርትራን የተመለከተ መፅሃፍ ሲፅፉ ይህ 28ኛው መሆኑ ነው። በዘውዴ ረታ የተጀመረው፣ ውበቱ ፀጋዬ ላይ አድርሶናል። ወደፊትም ኤርትራን በተመለከተ በየአመቱ ቢያንስ አንድ መፅሃፍ እንደሚፃፍ መገመት ይቻላል። ምክንያቱም ሊፃፍ ከሚገባው የኤርትራ የጦርነትና የፖለቲካ ታሪክ አንድ አምስተኛው እንኳ ገና አልተነካም።

የጄኔራል ውበቱን መፅሃፍ ገና አንብቤ አልጨረስኩም። ስጨርስ የተሟላ አስተያየት እፅፍበት ይሆናል። ለዛሬው ግን አንድ ሁለት ነጥቦችን ብቻ በጨረፍታ ላነሳ ወደድኩ።
ጄኔራል ውበቱ በመፅሃፉ መግቢያ ላይ “የኢትዮጵያ ሰራዊት በሻእቢያ ተዋጊዎች ለምን ተሸነፈ?” ለሚለው ጥያቄ ጥቂት ምክንያቶችን አስቀምጦአል። የመልከአምድር አቀማመጥ፣ ወታደሩ በቂ የተራራ ስልጠና አለማግኘት ወዘተ የመሳሰሉት አነስተኛ ምክንያቶች ናቸው። ዋናው ምክንያት ተብሎ የተቀመጠው ግን፣ “የምንዋጋው የህዝብ ድጋፍ ከነበረው ጠላት ጋር በመሆኑ...” የሚለው ነበር። (ገፅ 9) አያይዞም፣ የኤርትራ ህዝብ በጥቅሉ፣ እንዲሁም በኢትዮጵያ ሰራዊት ውስጥ የነበሩ ኤርትራውያን ከፍተኛ መኮንኖች ለሻእቢያ መረጃ ያቀብሉ እንደነበር ጠቅሶአል። ገበሬዎች ሳይቀሩ ሰራዊቱን በተሳሳተ መንገድ እየመሩ ለሻእቢያ ምቹ ሁኔታ በመፍጠር ያስደመስሱት እንደነበር ዘርዝሮአል።
ጄኔራል ውበቱ እውነት ብሎአል። ለዚህም ይመስላል እንደ ቀድሞው አጠራር የሻእቢያን ታጋዮች “ወንበዴዎች” ብሎ ለመጥራት አልፈለገም። “ተገንጣዮች” የሚል ቃል መጠቀሙን መርጦአል። ግዙፉን የደርግ ጦር አሸንፎ መንግስት ለመመስረት የበቃን ሃይል፣ “ወንበዴ” ማለት ከብዶትም ሊሆን ይችላል። ቢሆንም ውበቱ  ለ15 አመታት ኤርትራ መሬት ላይ ሲዋጋ የተጠቀመበትን ቃል ለመተው መወሰኑ ያስመሰግነዋል።
በሰላሳ አመቱ የጦርነት ዘመን ኤርትራውያን የነፃነት ትግሉ ደጋፊ በመሆን ለአማፅያኑ መረጃ ማቀበላቸውና  ገንዘብ እያዋጡ በምስጢር ወደ በረሃ መላካቸው እውነት ነው። ጄኔራል ውበቱ አላጋነነም። ሌላው ቀርቶ የጄኔራል ውበቱ የቅርብ የስራ ባልደረባ የነበረው ኮሎኔል እዮብ ገብረአምላክ ከስብሃት ኤፍሬም (ጄኔራል) ጋር ግንኙነት ፈጥሮ፣ የሰራዊቱን እቅዶች በሙሉ ለሻእቢያ ይልክ ነበር። (የስደተኛው ማስታወሻ - ገፅ 205) ርግጥ ነው፣ የመረጃ የበላይነት ያለው የማሸነፍ እድሉ ጠንካራ ነው።
ከጄኔራል ውበቱ መፅሃፍ በሁለተኛ ደረጃ የገረመኝ ነጥብም አለ።
የመፅሃፉ ምእራፍ ሁለት ከዋቆ ጉቱ ጋር የተደረገውን ጦርነት የሚዘግብ ነው። ውበቱ ፀጋዬ ወጣት ሻምበል ሳለ የዘመቻ መኮንን ሆኖ ባሌ ላይ በተደረገው ውጊያ ላይ መሳተፉን ዘግቦአል። በዋቆ ጉቱ እየተመሩ ባሌ ላይ ያመፁትን ኦሮሞ ገበሬዎች ጄኔራል ውበቱ፣ “ወንበዴዎች” እያለ ነበር የሚገልፃቸው። እዚህ ላይ ስደርስ ከፍ ባለ ድምፅ ስቄያለሁ። ሻእቢያ ስላሸነፈ ወንበዴነቱ ተሰረዘለት። ዋቆ ጉቱ ስላልተሳካለት ወንበዴነቱ ፀድቆ ቀረ። ዋቆ ጉቱ ቢሳካለት ኖሮ እንደ ጆሞ ኬንያታ ወይም በሳሞራ ማሼል ደረጃ ስሙ በተጠራ ነበር። ወንበዴነቱም በተሰረዘለት። ጄኔራል ውበቱ ስለ ዋቆ ጉቱ ምን ያህል እንደሚያውቅ አላውቅም። ስሙን እንኳ አስተካክሎ አልፃፈም። “ዋቆ ጉቶ” እያለ ነበር ያሰፈረው። ለመሳደብ ፈልጎ ይሁን የታይፕ ስህተት አላውቅም። ያም ሆነ ይህ ዋቆ ጉቱ ፍትሃዊ ጥያቄ ነበር ያነሳው። ሁዋላ ደርግ አጥጋቢ ምላሽ የሰጠበትን የቀላድና የገባር የመሬት ስርአትን ነበር የተቃወመው። ዋቆ ጉቱ የኦሮሚያን የመገንጠል ጥያቄ እንኳ ያነሳ አይመስለኝም። ጄኔራል ውበቱ ሻእቢያን “ወንበዴ” ለማለት ተሳቆ፣ የዋቆ ጉቱን ተከታዮች “ወንበዴዎች” ለማለት መድፈሩ ስላቅ ነበር የሆነብኝ። እና “ታሪክ የአሸናፊዎች ነው” የሚለውን አባባል ለማስታወስ ተገደድኩ።
ከኦሮሞ ወዳጆቼ ጋር ስንጨዋወት ብዙ ጊዜ የማነሳው አንድ ነጥብ አለ። በአፍሪቃ ቀንድ ባህልና ልማድ ክብር ለማግኘት የግድ ሃይል ያስፈልጋል። ሃይል ከሌለ ክብር የለም። ክብር ከሌለ ህይወት የለም። በአካባቢያችን በልመና ወይም በድርድር ክብርና ነፃነትን ማግኘት ህልም ነው። ማንዴላ ኢትዮጵያዊ ቢሆን ኖሮ ገና ድሮ ገድለን ቀብረነው ነበር። ስለዚህ በማንዴላ መንገድ ክብር ለማግኘት መሞከር የዋህነት ነው።
ጄኔራል ውበቱ የፖለቲካ ሰው አለመሆኑ በርግጥ ካልተደራጀውና በተቃርኖ ከተሞላው ፅሁፉ በቀላሉ መረዳት ይቻላል።ለመጥቀስ ያህል “ሻእቢያ ሙሉ የህዝብ ድጋፍ ነበረው” ብሎ ሲያበቃ፣ እልፍ ብሎ ደግሞ፣ “በኤርትራ ውስጥ ለአንድነት ሲባል ለ30 አመታት የተደረገው ጦርነት” እያለ ይቀጥላል።
የኤርትራ ህዝብ ከኢትዮጵያ ጋር አንድነት አለመፈለጉን ጄኔራል ውበቱ ካመነ፣ ኢትዮጵያ ያደረገችው ጦርነት ለአንድነት ሳይሆን ለወደብና ለመሬት ነበር ማለት ነው። ምክንያቱም “አንድነት” የሚለው ቃል ሰዎችን እንጂ መሬትን የሚመለከት አይመስለኝም። ዛሬም ድረስ አንዳንድ ፖለቲከኞች “ትግራይ ከፈለገች ትገንጠል። ድንጋይ ናት።” ሲሉ ይሰማሉ። የኦሮሚያና የኤርትራ ጉዳይ ሲነሳ ወደብና ቡናውን በማስታወስ ይንገበገባሉ። ህዝቡን ንቆ መሬት ለመያዝ የሚሞክር መቼም ቢሆን አይሳካለትም።
ጄኔራል ውበቱ ፀጋዬ የጦርሜዳ ልምዱን በመፃፉ ሊመሰገን ይገባዋል። ግልፅነቱ አያስወቅሰውም። ካልፃፉት እሱ ይሻላል። በኤርትራ ቆይታው የኤርትራ ህዝብ ላይ ጥላቻ እንዳልነበረው፣ በጥቅሉ ፕሮፌሽናል ወታደር እንደነበር በቅርብ የሚያውቁት ነግረውኛል። በድጋሚ ባርኔጣዬን አነሳለታለሁ።

7 comments:

Unknown said...

ይህ ሁሉ በኦሮሞ ስም የምትሰራው ሸፍጥ ትናንት በሻቢያ ማህጽን ተገላብጣ የሻቢያን ግት ጠብታ ለሀገር የበቃችውን ጨቅላዋን ሀገርህን ክፍ እንዳይነካት በማሰብ እንደሆነ ከማንም የተሰወረ ሀቅ አይደለም፡፡በአንተ መሰሉ ዘውግ አመላኪ ልቦና በኢትዬጲያ አንድነት መቃብር ላይ ጨቅላዋ ኤርትራ ለወግ ለማእረግ ትበቃለች የሚል አምክነዬ አምክነዬ ተደንቅራል፡፡
ለኦሮሞ ህዝብ እንዲህ ጭንቅ ጥበብ እንደምትለው ምነው የኤርትራ ሃማሴን ህዝብ ዘነጋሀው? መርዘኛው ብዕርህ አሁን አቅመ ቢስ ሆኖል፡፡ ከተራ አሉባላታ ያለፈ ስሜት መፍጠር ካቆመ........ሰነባበተ
ለወደፊቱ.... በቁቤ ብትጽፍ.ብዙ ዘውግ አምላኪዎችን አንጀት ማራስ ትችላለህ

ያሬድ ሄኖክ said...

ተስፍሽ ባንተ ዘመን በመፈጠሬ በጣም ደስተኛ ነኝ። እንኳን ከኛ ተፈጠርክ።እንኳንም በሩቅ የምናውቅህ ኣልሆነ። ባንተ በልጇ እና በሰፊው የኦሮሞ ህዝብ ትግል ኦሮምያ በቅርብ ቀን እራሷን በራሷ ታስተዳድራለች። የሚገርም እይታ ነው። እንዲህ እንዳንተ ኣይነት ተቆርቋሪ ኦሮምያ ያስፈልጋታል። የኦሮሞ ስም ይዘው የደብተራ ፍርፋሪ ፈላጊዎች ባሉበት ወቅት እንዲህ ኣይነት ልጅ በማግኘታችን ደስተኞች ነን። ሎሬትነት ሲያንስህ ነው። ያው ለተጨቆነው የኦሮሞ ህዝብ ስለጻፍክ እንጂ በችሎታህማ ድሮ ሎሬት ሊሉህ ይችሉ እንደነበር ግልጽ ነው ብዬ ነው። ለነገሩ ሎሬትነት የውጭ ባህል ነው። በራሳችን የኦሮሞ ባህል ሞጋሳ የተከበረው ገዳ ተብለህ የለም እንዴ?!

Anonymous said...

Hi,Gadaa( Tesfaye)
just after finished reading about Dr. Haile Fida on Oromedia came across your Blog's artcle.your bombasic pen obliged me to quote you here"በአፍሪቃ ቀንድ ባህልና ልማድ ክብር ለማግኘት የግድ ሃይል ያስፈልጋል። ሃይል ከሌለ ክብር የለም። ክብር ከሌለ ህይወት የለም። በአካባቢያችን በልመና ወይም በድርድር ክብርና ነፃነትን ማግኘት ህልም ነው። ማንዴላ ኢትዮጵያዊ ቢሆን ኖሮ ገና ድሮ ገድለን ቀብረነው ነበር። ስለዚህ በማንዴላ መንገድ ክብር ለማግኘት መሞከር የዋህነት ነው"። you are great to be quoted.who can tell that oldy Lenco and his bunches.

Anonymous said...

የኢትዮጵያ ታሪክ ከአክሱም ዘመነ መንግስት ጀምሮ እንደሆነ ይታሰባል፡፡ በተለየ ምክንያት ከአካባቢው ወደሌላ ቦታ የፈለሰ ህዝብ ስለመኖሩ በታሪክ እስካልተረጋገጠ ድረስ የአክሱም ታሪክ በቀጥታ የሚያያዘው በአካባቢው ከሚኖረው የትግራይና የደጋው የኤሪትራ ህዝብ ታሪክ ጋር እንደሆነ ይገመታል፡፡ ከአክሱም መውደቅ በኋላ ወደሥልጣን የመጣው የዛግዌ ሥርወ-መንግስትም የሚያያዘው ከአገው ህዝብ ታሪክ ጋር ነው፡፡ ከዚያ የጎንደር ሥርወ-መንግስትና የሁሉም ቅይጥ የሆነው የዘመነ-መሳፍት ይከተላሉ፡፡ ከዘመነ-መሳፍንት በኋላ ከአጼ ቴዎድሮስ ጀምሮ ያለው የዘመናዊ አገር ግንባታ ታሪክ ይመጣል፡፡ በዚህ የታሪክ ስሌት መሠረት የጎንደር የቅይጥ ሥርወ-መንግስትና የአጼ ቴዎድሮስ መንግስት ቅይጥነታቸው እንደተጠበቀ ሆኖ የአማራ ገዥ መደብ የሚባለው የአገርቷን ማእከላዊ ሥልጣን የያዘው ከአጼ ምኒልክ ጀምሮ ነው፡፡ ከዚያ ውጭ ያለው የነአጼ ልብነድንግልና ሌሎች አጼዎች አካባቢያዊ አስተዳደር ነበር፡፡

ከውጭ ጠላቶች በአገርቷ ላይ ከተቃጡት ጥቃቶች አንፃር ከታየም የአማራው ህዝብ በአብዛኛው ሰፍሮ የሚገኝበት አካባቢ በመልካ-ምድራዊ አቀማመጡ እምብዛም ለበርካታ ዓመታት ከውጭ በአገራቷ ላይ ከተቃጡት ጦርነቶችና ጥቃቶች ጋር የሚገናኝ ባለመሆኑ /ከድርቡሽ ወረራ በስተቀር እሱም ቢሆን ከፍተኛውን መስዋእትነት የከፈለው ከአጼ ዮሐንስ 4ኛ ጋር የዘመተው የትግራይ ጦር መሆኑ እንዳለ ሆኖ/ የአማራ ህዝብ የውጭ ጥቃት ቀጥታ ገፈታ ቀማሽ አልነበረም፤ አገርቷን ከውጭ ጠላት ጥቃት በመከላከሉም በኩል አማራው ለብቻው በተለየ ሁኔታ ያደረገው ልዩ አስተዋጽኦ በታሪክ ተመዝግቦ አይገኝም፡፡ በዚህ በኩል ታሪክ የሚያረጋግጠው እንዲሁም ከመልካ-ምድራዊ አቀማመጣቸው የተነሳ የትግራይና የኤሪትራ፣ የሶማሊና የአፋር ህዝቦች ብዙ ዋጋ የከፈሉ መሆናቸውን ነው፡፡

የአድዋ ጦርነትም ቢሆን የተካሄደው በትግራይ በመሆኑ በጦርነቱ የተጎዳው የትግራይ ህዝብ የነበረ ሲሆን፣ ጦርነቱን የመሩት አጼ ምኒልክ ቢሆኑም የተዋጉት ደግሞ ሁሉም ኢትዮጵያን በመሆናቸው ድሉም የሁሉም ነው፡፡ የአገር ውስጥ ቅርቋሶች የግራኝ አህመድን እንቅስቃሴ ጨምሮ ሥልጣን ለመያዝና በላይነትን ለማረጋገጥ የሚካሄዱ የእርስ-በርስ የውስጥ ጦርነቶች ስለነበሩ አገርቷን ከጥቃት እንደመከላከል ሊወሰዱ የሚችሉ አይደለም፡፡

ታዲያ የአገርቷ ታሪክ በተጨባጭ የሚያረጋግጠው ይህን ሆኖ ሳለ የአማራ ህዝብ ብቻ ለኢትዮጵያ እንደአገር መፈጠርና እንደአገር ተጠብቃ መቆየት መስዋእትነት ሲከፍል እንደኖረና በዚህም የተነሳ አማራው በውስጥም በውጭም ካሉት ጠላቶች ጥርስ እንደተነከሰበት በኢትዮ-አማሮች የሚሰበከው ከምን የመጣ ነው? ወይስ ታሪክ ማእከላዊውን ሥልጣን ይቆጣጠር የነበረው ኃይል ታሪክ የሚባለው መሆኑ ነው? ተስፋዬ፣ እባክህን በዚህ ጉዳይና ሰለሞናዊ ሥርወ-መንግስት በሚባለው ነገር ላይ ሰፋ ያለ ጽሑፍ ቢታወጣበት ለሁሉም ግንዛቤ የሚጠቅም ይመስለኛል፡፡ መልካም ጊዜ!

Anonymous said...

Ante rasih zewg amlaki batihon noro endezi atilim neber. The only difference is you are hiding behind Ethiopia. Hagerawi agenda sayihon zewgawi agenda new yaleh. If his audience should only be Oromos as you say, the only reason you don't like his writings is because you are....

Anonymous said...

Tesfaye I will assure you that your dream never come true, Ethiopia is becoming strong nation in all direction, I wonder why you have such hate to Ethiopia?

asba said...

ሰላምና ጤና ተስፋዬ ከመጽሃፎቸሀ ዉስጥ ሁሰት ያህሉን አንብቤያለሁ፡እውነትን የሚናገሩ ሁሌ ክብር አላቸው፡፡፡ ክብር ይገባሃል፡፡በርታ፡፡